(ዘ-ሐበሻ ዜና) አትሌት ሩቲ አጋ በዶፒንግ ጊዜያዊ እገዳ ተጣለባት፡፡ የ32 አመቷ ኢትዮጵያዊት የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ሩቲ አጋ ላይ ጊዜያዊ እገዳ መጣሉን የአለም አትሌቲክስ የፀረ ዶፒንግ ተቋም አስታወቀ፡፡ በአትሌቷ ላይ እገዳው የተጣለው ‹‹ሜልቲፕሬድኒሶሎን›› የተባለ በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር በሰውነቷ ውስጥ በመገኘቱ እንደሆነም ገልጿል፡፡
እንዲሁም በምርመራ ሂደት ጣልቃ በመግባትም ክስ ያቀረበባት ሲሆን እገዳው ጊዜያዊ እንደሆነና ይግባኝም ማቅረብ እንደምትችል አስረድቷል፡፡ አትሌቷ በማራቶን፣ በግማሽ ማራቶን፣ በ10 ሺህ እና በ5 ሺ ሜትር ውድድሮች ጥሩ ሰአት ያላት ናት፡፡ ‹‹ሜልቲፕሬድኒሶሎን› የተሰኘው ንጥረ ነገር በአለም አቀፉ ፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲ በውድድር ወቅት የተከለከለ ንጥረ ነገር ቢሆንም በተለያዩ ላብራቶሪዎች በተደረገ ጥናት በአካል ብቃት ላይ ያን ያህል ለውጥ የሚያመጣ አይደለም፡፡

24 days ago