Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፣ የእስራኤል ጦር እና የ'ሺን ቤት' (የሀገር ውስጥ ደህንነት) ኃይሎች የ"የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን" የራፋህ ብርጌድ አዛዥ መግደላቸውን አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባወጡት መረጃ እንዳስታወቁት፣ የተገደለው አዛዥ በእስራኤል ኃይሎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እቅድ ሲያወጣ እንደነበር ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና የእስራኤል ኃይሎች በደቡብ ሊባኖስ ቢያንስ በሦስት አካባቢዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸማቸውን የሊባኖስ ይፋዊ የብሔራዊ ዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።

ኤጀንሲው እንዳስረዳው ማይፋዱን አቅራቢያ በሚገኘው አይን አል-ሰማሂያህ በተባለው ወረዳ ላይ ሁለት ተከታታይ የአየር ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በተጨማሪም የእስራኤል የአየር ጥቃቶች በጢሮስ ቀጠና በሚገኘው የዋዲ ዚብቂን አካባቢ እንዲሁም በማርጃዩን አካባቢ ላይ ማነጣጠራቸው ተገልጿል።

25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.