ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
ብሔራዊ ትርክት፡ የነገዋን ጠንካራ የጋራ ኢትዮጵያ ለመገንባት
ኢትዮጵያ በቀደሙት ጊዜያት አሰባሳቢ ገዢ ትርክት መገንባት ባለመቻሏ ምክንያት ሕልውናዋ እና ሀገራዊ አንድነቷ ለአደጋ ተጋልጦ ቆይቷል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በመደመር መንግሥት እሳቤ የተዛቡ ትርክቶችን ከመሠረታቸው የሚቀይሩ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል።
ሀገር የትርክት ውጤት በመሆኑ ቅቡልነት ያለው ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የገዢ ትርክት ግንባታ በልዩ ትኩረት እየተሰራበት ይገኛል።
የወል ትርክት በማህበረሰብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ የተቋማት ግንባታን በማሳለጥ፣ ሀገራዊ ትልሞችን፣ ርዕዮችን፣ ማህበራዊ ትስስርን ለማሳደግ እና ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠርም ወሳኝ ሚና አለው።
ከመራራቅ ይልቅ መቀራረብን፣ ከጥርጣሬ ይልቅ መተማመንን በማጎልበት የተዛቡ ትርክቶችን ማረምና ማስተካከል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው።
በተዛባ ትርክት የተፈጠረውን የትውልድ ዕዳ በመክፈል ለመጪው ትውልድ ምንዳ እንጂ ዕዳ ላለማውረስ ብርቱ ትግል ተጀምሯል።
ገዢ ትርክት ሕብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክርና የነገዋን የጋራ ኢትዮጵያ በመገንባት የኢትዮጵያውያንን አንድነት የሚያጎላ ነው።
እንዲሁም ዜጎች በሀገር ጉዳይ ላይ በጋራ እንዲቆሙ እና ለብልጽግና እንዲተጉ በማድረግ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት የጋራ መግባቢያ መንገዶችን ይከፍታል።
የመደመር መንግሥት ሕብረብሔራዊነትን በማጎልበት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።
የተሳሳቱና የተዛቡ ትርክቶችን በማረም ሕብረብሔራዊ አንድነትን መገንባት ሀገራዊ ልዕልናን ለማብሰር ጠቀሜታው ከፍተኛ ሲሆን÷ በወል ትርክት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ይቻላል።
ሀገር በመግባባት ላይ የምትገነባ የወል ቤት በመሆኗ የወል እውነትን መነሻ ያደረጉ ገዢ ትርክቶች መገንባት ያስፈልጋል፤ ሕብረብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና በወል እውነት የጸናች፣ ከፍታዋ የተረጋገጠ የጋራ ሀገር ለመገንባት ብሔራዊ ገዢ ትርክት ወሳኝ ነው።
መደመርና አብሮነት የኢትዮጵያውያን እሴት በመሆኑ አንድነትን የሚያጎለብቱ የጋራ ትርክቶች ላይ በማተኮር ለሀገራዊ ልዕልና መትጋት የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ሊሆን ይገባል፡፡

26 days ago