(ዘ-ሐበሻ ዜና) የየመን ታጣቂዎች ‹‹በ5 ቀን ውስጥ ከ300 በላይ ጥቃት ተፈፅሞብናል›› አሉ፡፡ በየመን የሚንቀሳቀሱትና በኢራን የሚደገፉት የሁቲ ታጣቂዎች ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ ከ300 በላይ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው አስታወቁ፡፡ የታጣቂዎቹ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሪ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስረዱት የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ኤፍ 15 እና ታይፎን ተዋጊ ጀቶችን በመጠቀም ባለፉት 5 ቀናት ውስጥ በየመን የተለያዩ ግዛቶች ድብደባ ፈፅሟል፡፡
ለእነዚህ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ጥቃቶች ዛሬ መልስ መስጠታቸውንም አስረድተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በሳኡዲ አረቢያ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው ካሚስ ሙሻይት ከተማ በሚገኝ የአየር ሀይል ጦር ሰፈር ላይ በሚሳኤልና በድሮኖች ጥቃት መፈፀማቸውን አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ጥቃትም በአውሮፕላን መጋዘኖችን፣ ራዳሮችን፣ መንደርደሪያዎችን፣ የጥይት ማከማቻዎችንና ሌሎች ወታደራዊ ተቋማትን መምታታቸውን ጠቅሰው በጦር ሰፈሩ ላይ ‹‹ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል›› ብለዋል፡፡
በንጉስ ካሊድ የአየር ሀይል ጦር ሰፈር ላይ ይህ ጥቃት መድረሱን አናዱሉ የዜና አውታር የዘገበ ቢሆንም ቃል አቀባዩ ‹‹ደረሰ›› ስላሉት ጉዳት ግን ከገለልተኛ አካል የተባለ ነገር የለም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የካሚስ ሙሻይት ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በከተማው ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ‹‹አደጋ›› ማለፉን የጠቀሰ ሲሆን ነዋሪዎች ፎቶና ቪዲዮ ከመቅረፅ እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

26 days ago