(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢራን ‹‹በየመን ጦርነት ምንም ተሳትፎ የለኝም›› አለች፡፡ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባቃይ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አገራቸው በየመን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንዳልገባችና አሁን ባለው ሁኔታ ላይ ምንም ተሳትፎ እንደሌላት ገለፁ፡፡
ቃል አቀባዩ ሲናገሩ ‹‹የሁቲ ታጣቂዎች በራሳቸው ነፃነት የሚንቀሳቀሱና የራሳቸውን አላማ ለማሳካት ራሳቸውን ችለው ውሳኔ የሚያሳልፉ ናቸው›› ብለዋል፡፡ የባህረ ሰላጤው አገራት በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ለመምከር የነበራቸው ቀጠሮ በየመን ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ መራዘሙንም አስረድተዋል፡፡ በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ኢራንና የመን ሀላፊነትን የያዘ የጋራ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ ዛሬ በኦማን ሊደረግ ታቅዶ የነበረው ስብሰባ ይህንን ውሳኔ ለቀጠናው አገራት ማሳወቅን ያለመ እንደነበርም ገልፀዋል፡፡

26 days ago