ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በታዋቂው "ታይም" መጽሔት የፊት ገጽ ላይ ሽፋን አገኘ
የዓለማችን ግዙፍና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የሕትመት ውጤቶች አንዱ የሆነው «ታይም» መጽሔት፣ የመስከረም 2026 ዕትሙን የፊት ገጽ ሙሉ በሙሉ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሰጥቷል። መጽሔቱ በሽፋን ገጹ ላይ «አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል» (The Power to Unite Africa) የሚል ታላቅ ዋና ርዕስ በመስጠት፣ ግድቡ በአህጉሪቱ ላይ እያሳደረ ያለውን መልካም ተፅዕኖ በስፋት ዳስሷል።
«ታይም» መጽሔት ባወጣው ሰፊ ዘገባ፣ የሕዳሴው ግድብ ለአህጉራዊ ትስስርና ለምስራቅ አፍሪካ አዲሱ የኢኮኖሚ ውህደት ምዕራፍ እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና በምሳሌነት ጠቅሷል።
ግድቡ የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ፣ ለአጠቃላይ የአፍሪካ አህጉር የቀጣናው ትስስርና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዋነኛ መሠረት መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።
በተጨማሪም፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በምስራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የኃይልና የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ በማጠናከር፣ በአህጉሪቱ አዲስ የትብብር፣ የልማትና የእድገት ምዕራፍ መክፈቱን መጽሔቱ በዕትሙ በዝርዝር ማስፈሩን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።
ግድቡ በአፍሪካውያን የራሳቸው ካፒታልና ጽናት የተገነባ መሆኑ አህጉሪቱ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን አቅም እንዳላት ያሳየበት ትልቅ ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።
Seledadotio

27 days ago