የአምስቱ ጋዜጠኞች ውሳኔ እና የሲፒጄ ጥሪ‼
በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ምንም አይነት ወንጀል ስላልፈጸሙ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲፈቱ የቀረበላቸውን ሀሳብ አለመቀበላቸውን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ወይም ሲፒጄ አስታውቋል።
ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ ሲሆኑ በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2023 የተያዙ ናቸው። ከዚያም በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰሰው የፍርድ ቤት ሂደታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ እንደገለጹት የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋዜጠኞቹን ከሌሎች ታሳሪዎች በመለየትና በማስፈራራት መንግስት ያዘጋጀውን የይቅርታ ወረቀት ፈርመው ከእስር እንዲወጡ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ስራቸውን እንዲተዉ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር።
ነገር ግን ጋዜጠኞቹ ምንም ያጠፉት ጥፋት በሌለበት ሁኔታ ራሳቸውን እንደ ወንጀለኛ አድርገው መቁጠርና ማመንን ባለመቀበል የቀረበላቸውን ጥያቄ ፈፅመው ውድቅ አድርገውታል ብለዋል።
የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞቹን ለረጅም ጊዜ ካሰሩ በኋላ በፍርድ ቤት ማረጋገጥ ያልቻሉትን ወንጀል በግዴታ አምነው እንዲቀበሉ ለማድረግ የሚያደርጉትን አካሄድ ኮንነዋል።
አስተባባሪዋ አክለውም በጋዜጠኞቹ ላይ የሚፈጸመው ያልተገባ ጫና በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የተመሰረተባቸው ክስ ተነስቶ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንዲሁም ሙያቸውን በነጻነት ማከናወን እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል።
Seledadotio

28 days ago