አበባዬሆሽ፤ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ ባህላዊ ዜማ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተፈጥሮ መታደስ፣ የደማቅ አበቦች መፈንዳትና የክረምቱ ጨለማ ማለፍ ሲበሰር በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አብሮ የሚመጣ አንድ ትልቅ ባህላዊ እሴት አለ። እርሱም አበባዬሆሽ ነው።
የአበባዬሆሽ ጨዋታ በሴት ልጃገረዶች የሚዘወተር፣ ትውልድን ከትውልድ ያሻገረ ውብ የዘመን መለወጫ ጨዋታ ሲሆን÷ ልጃገረዶች መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋንና ብርሃንን ይዘው ለሕብረተሰቡ የምስራች ይናገራሉ።
ይህ ጨዋታ ሴት ልጆች በነፃነት የሚደሰቱበት፣ የፈጠራ አቅማቸውን የሚያሳዩበት እና በአካባቢያቸው ላይ የበዓል ድባብን የሚፈጥሩበት ልዩ መድረክ ነው።
እነዚህ ልጃገረዶች የሚጫወቱት የዜማ ውበት በአካባቢው ላይ ልዩ የበዓል ድባብን በመፍጠር የአዲስ ዓመት መምጣትን የመስከረም መጥባትን ያስተጋባል።
በሚጫወቱበት ወቅትም የቤቱን ባለቤቶች ስም እየጠሩ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ለአባወራው ጤናና ሀብት፣ ለእማወራዋ ደግነትና ምርታማነት፣ ለልጆቹ ደግሞ ስኬትን በግጥሞቻቸው ይመኛሉ።
የቤቱ ባለቤቶችም የልጆቹን መምጣት በደስታ ተቀብለው የአበባዬሆሽ ጭፈራቸውን ካዳመጡና ከመረቁ በኋላ እንደየአካባቢው ባህል የተለያዩ ስጦታዎችን ያበረክታሉ።
በባህላዊ ሥርዓቱም ልጆች በአንድነት መስራትን፣ እርስ በርስ መተሳሰብንና አብሮነትን ይማሩበታል። እንዲሁም በጎረቤቶችና በነዋሪው መካከል ያለውን ትስስር፣ ፍቅርና መከባበር ለማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
አበባዬሆሽ ተራ የልጆች ጨዋታ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን ባህላዊ ማንነት፣ የሴት ልጆችን ጥበብና ተሳትፎ እንዲሁም የተፈጥሮንና የሰው ልጅን መስተጋብር የሚያሳይ ባህላዊ ክዋኔ ነው።
አበባዬሆሽ በሴት ልጆች (ልጃገረዶች) ብቻ የሚከናወን ትውልድን ከትውልድ ያሻገረ፣ ጥልቅ ማህበራዊና ጥበባዊ ፍልስፍና ያለው ውብ የዘመን መለወጫ ባህል ነው፡፡
ይህንን ውብ ባህል ጠብቆ ማቆየትና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሁላችንም ድርሻ ነው።
በትዕግስት ግዛቸው

29 days ago