Logo
SeledaPost
በኤራትራ በወጣ አዲስ መመሪያ ግለሰቦች ከ25 ሺህ፣ ተቋማት ከ150 ሺሕ ናቅፋ በላይ ጥሬ ገንዘብ በእጅ እንዳይዙ ታዘዘ።

የኤርትራ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ከባንክ ሥርዓት ውጭ ለተወሰነ ጊዜ መያዝ የሚችሉትን የጥሬ ገንዘብ መጠን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ማውጣቷን የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

በአገሪቱ መንግሥታዊ የሕግ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ይፋ በተደረገው መመሪያ፣ ማንኛውም ዓይነት የኤርትራ ገንዘብ፣ ናቅፋ ዝውውር በባንኮች እና በገንዘብ ተቋማት ብቻ መሆን እንዳለበት ያዛል።

መመሪያው ግለሰቦች ከ25 ሺህ ናቅፋ በላይ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ከ15 ቀናት በላይ በእጃቸው ማቆየት እንደማይችሉ ገደብ ጥሏል።

እንዲሁም በተለያዩ ሦስት ደረጃዎች የተመደቡ የንግድ ተቋማትም በ50 ሺህ፣ በ100 ሺህ እና በ150 ሺህ ናቅፋ መጠን የተገደበ ጥሬ ገንዘብ ለሁለት ሳምንታት ብቻ መያዝ እንዲችሉ ተፈቅዷል።

ከተፈቀደላቸው የጥሬ ገንዘብ መጠን እና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ ተቀባይነት ካለው ምክንያት ውጭ ይዘው የተገኙ ተቋማትና ግለሰቦች #ሕጋዊ_እርምጃ " እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል።

አሁን የኤርትራ ማዕከላዊ ባንክ ያወጣው በግለሰቦች እና በተቋማት ይዞታ ስር ሊቀመጥ የሚችልን የገንዘብ መጠንን የሚገድበው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ነው።

የመዋዕለ ነዋይ ዘርፍ በመንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ሥር በሚገኘባት ኤርትራ በጥሬ ገንዘብ መገበያየት ዋነኛው እና በስፋት ጥቅም የሚውል ነው። የባንክ አገልግሎቶች በመላዋ አገሪቱ የተስፋፋ አይደለም።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.