በአርባ ምንጭ በሕገወጥ መጋዘን የተከማቹ መድኃኒቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኝ ሕገወጥ መጋዘን ውስጥ የተከማቹ በርካታ ያልተፈቀዱ መድኃኒቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ አስታወቀ።
ኦፕሬሽኑ የተካሄደው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ ከከተማው ጤና መምሪያ እና ፖሊስ ጋር በመተባበር በተደረገ ሰርቬላንስ ነው።
ከተያዙት መካከል እንደ ትራማዶል እና አድሬናሊን ያሉ በመርፌ የሚሰጡ መሠረታዊ መድኃኒቶች ይገኙበታል። መድኃኒቶቹ ጥራታቸው ያልተረጋገጠ እና የገበያ ፈቃድ የሌላቸው ናቸው።
ድርጊቱ በህብረተሰብ ጤና ላይ ሊደርስ የነበረውን አደጋ ያስቀረ ሲሆን፣ በጥፋተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል። ባለሥልጣኑ ህብረተሰቡ መሰል ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
Seledadotio

1 month ago