የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጣራ ትርፍ በ75.8% ማደጉን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ በኋላ የሚያገኘውን የተጣራ ትርፍ በ75.8% በማሳደግ 38.71 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ይፋ በተደረገው የኦዲት ሪፖርት ላይ ገለጸ።
በባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አህመድ ሽዴ እና በፕሬዚዳንቱ አብይ ሳኖ የጸደቀው የኦዲት አገልግሎት ኮርፖሬሽን ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ የተቋሙ የወለድ ገቢ በ30.7% አድጎ 132.06 ቢሊዮን ብር ደርሷል። በሌላ በኩል የባንኩ የወለድ ወጪዎች በ1.8% ብቻ አድገው 45.31 ቢሊዮን ብር መሆናቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ ከወለድ ውጭ ያለው ገቢ በ77.5% እድገት በማሳየት 60.52 ቢሊዮን ብር መድረሱ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ሆኖም የሰራተኞች እና ሌሎች የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች በእጥፍ በመጨመር 113.71 ቢሊዮን ብር መድረሳቸው ተጠቁሟል።
Seledadotio

1 month ago