ለአዲስ ዓመት የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተከናውኗል ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ህብረተሰቡ በደስታና በመረጋጋት እንዲያከብር የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ሰፊ የቅድመ ዝግጅትና የጥገና ሥራ ማከናወኑን ገልጿል።
በአዲስ ዓመት በዓል ወቅት የሚያጋጥሙ የኃይል ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ 24 ሰዓት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክ ቡድን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀት ወደ ሥራ መግባቱን ተቋሙ ተናግሯል።
በተጨማሪም በሁሉም የአገልግሎቱ ሪጅኖችና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አጣዳፊ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ የጥገና ቡድኖች ተደራጅተዋል። በዚህም በነሐሴ ወር በመላ አገሪቱና በአዲስ አበባ 2 ሺህ 110 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ የኃይል መስመር ተፈትሿል።
በፍተሻው የተለዩ 10 ሺህ 308 የኃይል መቆራረጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮችም ተስተካክለዋል ተብሏል። ከ8ሺህ በላይ ትራንስፎርመሮች የተፈተሹ ሲሆን በ6 ሺህ 877 ትራንስፎርመሮች ላይ የተለዩ የቴክኒክ ችግሮች ተፈትዋል።
በበዓሉ ዋዜማ ሊከሰት የሚችለውን ተጨማሪ የኃይል ጭነት ለመቋቋምም 178 ትራንስፎርመሮች አቅማቸው ተሻሽሏል። በተጨማሪም ከ3 ሺህ በላይ ትራንስፎርመሮች የዘይት መሙላትና የጥገና ሥራ ተደርጎላቸዋል። በበዓሉወቅት ለሚያጋጥሙ ድንገተኛ የኃይል ችግሮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም 24 ሰዓት የሚሰሩ የቴክኒክና የጥገና ቡድኖች መዘጋጀቱን የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዋር አብራር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ተቋሙ በበዓሉ ወቅት ደንበኞች ኃይል ቆጣቢ ቁሳቁሶችን እንዲጠቀሙና የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶቻቸውን ለአደጋ እንዳያጋልጡ ጥሪ አቅርቧል። የኤሌክትሪክችግር ወይም የጥገና ጥቆማ ሲኖር ደንበኞች በ905 በነፃ በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ ሲሉ አቶ አንዋር አብራር ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Seledadotio

1 month ago