ኬንያ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ለሌላቸው #የምስራቅ_አፍሪካ ዜጎች ጊዜያዊ ምሕረት ሰጠች
ኬንያ ከውጭ አገር በመጡ አነስተኛ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የቡሩንዲ ዜጎች ሰኞ ዕለት በናይሮቢ ወደሚገኘው የአገራቸው ኤምባሲ የጉዞ ሰነዶችን ፍለጋ በሄዱበት ወቅት ነው የኬንያ መንግሥት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ለሌላቸው የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች ጊዜያዊ ምሕረት የሰጠው።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በባለፈው ሳምንት ከታክስ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ካቀረቡ የኬንያ ነጋዴዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ፣ ባለሥልጣናት ከሰኞ ጀምሮ በውጭ አገር ነጋዴዎች የሚካሄዱ ሁሉንም አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲዘጋ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።
የኬንያ ንግድ ሚኒስቴር ያለ ሥራ ፈቃድ በሚሰሩ የውጭ አገር ዜጎች ላይ እንደሚተገበር የተናገረው ይህ ትዕዛዝ፣ ሰኞ እለት በቡሩንዲ ኤምባሲ ውጭ ሁከትና ብጥብጥ የቀሰቀሰ ሲሆን፣ የቡሩንዲ ዜጎች የሩቶን ንግግር ተከትሎ ከጎረቤቶቻቸው ማስፈራሪያ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ሰኞ ዕለት በናይሮቢ ምንም አይነት የእርምጃ ምልክቶች ያልታዩ ሲሆን፣ የሩቶ አስተዳደር ቃል አቀባይ በኋላ እንደተናገሩት፣ መንግሥት ማንኛውንም አይነት ትንኮሳ፣ ማስፈራራት ወይም የውጭ ዜጎች ጠልነትን በፍጹም የመታገስ ፖሊሲ እንደሌለው ገልጸው፣ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የምስራቅ አፍሪካ አገራት ዜጎች፣ በተለይም የቡሩንዲ ዜጎች በኤምባሲዎቻቸው ሕጋዊ ምዝገባ እንዲያካሄዱ አሳስበዋል።
"በዚህ በተወሰነው የምዝገባ ወቅት፣ ምዝገባ የሚያካሄዱ ግለሰቦች በኬንያ ሪፐብሊክ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ እንደተገኙ ይቆጠራሉ።
Seledadotio

1 month ago