Logo
SeledaPost
ለአዲስ አመት ከ4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳትን ተዘጋጅተዋል

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የዘንድሮውን የአዲስ አመት በዓል  አስመልክቶ ትላንት ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ተቋሙ በመጪው የአዲስ ዓመት በዓል 4 ሺህ 500 የቁም የእንስሳትን እርድ  ለማከናወን  ዝግጅት አጠናቋል።

ከእነዚህም መካከል ከ3 ሺህ በላይ በሬዎች እና ከ1 ሺህ 500 በላይ በግና ፍየሎች እርድ እንደሚከናወን ተገልጿል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በግና ፍየልን በ300 ብር፣ እንዲሁም በሬዎችን ደግሞ በ2ሺ 100 ብር የቄራ የእርድ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የተጠቀሰው።

ሕብረተሰቡ ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ ሥጋዎችን  እንዲያገኝ ወደ ቄራዎች ድርጅት መምጣት እንደሚገባው ጥሪ ቀርቧል።

በበዓሉ የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል በአዲስ አበባ በሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች 1 ኪሎ የበሬ ሥጋ 1 ሺህ 200 ብር ሆኖ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተቋሙ ገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.