Logo
SeledaPost
ኢትዮ ቴሌኮም  ከ188 ሚ ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም «በበጎነት» እና «ለነገ ተስፋዎች» መርኃ ግብሮች በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ 50 የበጎ አድራጎት ተቋማት እና ከ105 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ188 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። በዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራው ይህ ማህበራዊ ኃላፊነት ማስፈጸሚያ መርሃ ግብር 22 ሺህ አረጋውያን፣ ሕፃናት እና አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን፣ ኩባንያው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥም በርካታ ተቋማትን መደገፉን አስታውሷል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ «በጎነት ለሰብዓዊነት» በሚል መሪ ቃል ከብሔራዊ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር የሥራ ኃላፊዎችና በጎ ፈቃደኛ ሠራተኞች በ22 የተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ደም ለግሰዋል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.