Logo
FastMereja
ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በዛሬው እለት ተማሪዎችን አስመረቀ!

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም. የትምህርት መርሀ ግብር ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በቴክኒክና ሙያ መርሀ ግብር በማስተማር ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ያስመረቀው።

የ23 ዓመታት ዓመታት የሥራ ልምድ ያለዉ ና ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ እና ከአዲስ አበባ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት፣ የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለሥልጣን የሚሰጠውን እውቅና ፈቃድ በመውሰድ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሁለተኛ ዲግሪ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በቴክኒክን ሙያ ሥልጠና የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልደት አዳራሽ ለምርቃት አብቅቷል፡፡

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ በተለያዩ ማህበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ተቋማዊ ግዴውን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

ከነዚህም መካከል አሂድ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር 120 ወገኖች የነጻ ትምህርት እድል በማመቻቸት በዛሬው ዕለት እንዲመረቁ አድርጓል፡፡

በዛሬው ዕለት በአበበ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልደት አዳራሽ በተከናወነው የምረቃ ፕሮግራም የተከበሩ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልሳን ትምህርት ከፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የተከበሩ ዶ/ር ኃየሎም ባንትይርጋ የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ በክብር እንግድነት ተገኘተው በቅደም ተከተል ለተመራቂዎች የሙያና የሕይወት ተሞክሮሯችሁን በመግለጽ ለተመራቂ ተማሪዎች መልእከት አስተላልፈዋል፡፡

በዛሬው የምረቃ በዓል በማስተርስ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር እና በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ዘርፍ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ፡-

የ2018 የሁለተኛ ዲግሪ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እና የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች በቴክኒክና ሙያ ወንድ 151 ሴት 493 ድምር 644፣ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር ወንድ 736 ሴት 1,764 ድምር 2,500

በሁለተኛ ዲግሪ መርሐ ወንድ 17 ሴት 15 ድምር 32 አጠቃላይ ድምር በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ 3176 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.