“በፌዴሬሽን ቲኬት ከሀገር ወጥቼ አላውቅም” — ኢሳያስ ጅራ
ከሰሞኑ ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ለፕሬዝዳትነት ቀርበው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፌዴሬሽኑ አመራርነት በነበሩበት ጊዜ ለውጭ ጉዞዎቻቸው የተጓጓዥ ቲኬት ወጪ በፌዴሬሽኑ ተሸፍኖላቸው እንደማያውቅ ገለጹ።
ኢሳያስ ጅራ ይህን የተናገሩት ከኢቲቪ “ስለ ስፖርት” ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ሲሆን፣ በፊፋ እና በካፍ በሚያከናውኗቸው ኃላፊነቶች ምክንያት የውጭ ጉዞዎቻቸው ወጪዎች በእነዚህ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተቋማት እንደሚሸፈኑ አስረድተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው የኢትዮጵያን እግር ኳስ መምራት ፈታኝ እንደሆነም ገልጸዋል። በተለይም ብሔራዊ ቡድኑ የሚጠበቀውን ውጤት ሳያስመዘግብ ሲቀር ማየት እንደሚከብዳቸው አስረድተዋል። ኃላፊነቱ የሀገር ጥሪ ቢሆንም፣ በሕዝቡ የሚጠበቀው ውጤትና በሜዳ የሚመዘገበው ውጤት መራራቁ የፌዴሬሽኑን አመራር ከባድ እንዳደረገው ኢሳያስ ጅራ ገልጸዋል።
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ለ8 አመታት በፕሬዝዳንት እግር ኳስ ፌደሬሽኑን የመሩት አቶ ኢሳያስ አዲስ ለውጥ በሚፈልጉ ስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ተቀባይነታቸው ዝቀተኛ መሆኑን በፕሬዝዳንትነት የምርጫ ወቅት ጊዜ ተቀናቃኞቻቸው ሲያነሱ ቢቆዩም ለእጩነት የቀረበ ሌላ ተወዳዳሪ ባለመገኘቱ ለተጨማሪ 4 አመታት በአመራርነት እንዲቆዩ ተመርጠዋል።

1 month ago