ጋሞ ጎፋ፣ አርባምንጭ…
ከአዲስአበባ ተነስተን ከ 450 ኪ.ሜ በላይ ተጉዘን አርባምንጭ ላይ ተከስተናል
አትሌቲክስና ቲያትር…
አንዱ በሜዳ ላይ ሰውነትን ይፈትናል፤ ሌላው በመድረክ ላይ ስሜትን።
አንዱ ለአንዲት ሰከንድ ውጤት ዓመታትን ይለማመዳል፤ ሌላው ለጥቂት ሰዓታት ትዕይንት ወራትን ይዘጋጃል።
ሁለቱም ግን አንድ ነገር ይጋራሉ ተሰጥኦ፣ ትጋት፣ ዲሲፕሊንና ለሕዝብ ስሜት መስጠት።
ስፖርት ሰውነትን ያንቀሳቅሳል፤ ጥበብ ነፍስን።
አትሌቲክስ ሜዳ ላይ ታሪክ ይሰራል፤ ቲያትር መድረክ ላይ ሕይወትን ይናገራል።
አርባምንጭ የሀይቆቿ ሰማያዊ ውሃ፣ የተፈጥሮዋ አረንጓዴ ልብስ ከተማዋን ልዩ ያደርጓታል።
ከአትሌቲክስ ስፖርት ጋር የተያያዘ ሕይወት ቢኖረኝም፣ ከስፖርት ውጪ በልቤ ልዩ ቦታ ያለው ጥበብ "ቲያትር" ነው።
ቲያትር ሕይወት ነው፤ ፍቅር ነው፤ ስሜት ነው። በጥቂት ቃላት ሰውን ማሳቅ፣ ማስለቀስ፣ ማሰብና ራሱን እንዲመለከት ማድረግ የሚችል ድንቅ የሰው ልጅ ጥበብ ነው።
ዛሬ ደግሞ በአንጋፋው ደራሲና አዘጋጅ ተሻለ ወርቁ የተዘጋጀውን “ፍሬው” ቲያትር ለመታደም አርባምንጭ ተከስተናል።
በተለይም የአገራችን አንጋፋና ታዋቂ አርቲስቶች በአንድ መድረክ መሰባሰባቸው ይህንን ትዕይንት የበለጠ ልዩ ያደርገዋል።
11:00 በኦሞ አዳራሽ እንገናኝ !
አርባምንጭ የተፈጥሮ፣ የስፖርትና የጥበብ ውብ ገጠመኝ!

1 month ago