(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጣሊያን በኢትዮጵያና ግብፅ መሀከል ሽማግሌ ሆና መስራት እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡ የጣሊያን መንግስት በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል በአባይ ወንዝ ዙሪያ የተፈጠረውን ውዝግብ በውይይት ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡ ይህንን የገለፁት የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ በካይሮ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ነው፡፡
በጉብኝታቸው ከግብፅ አቻቸው በድር አብደል አቲ ጋር በመሆን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በአባይ ወንዝ ላይ ድርድር አድርጎ መፍትሄ ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው›› ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህም በአለም አቀፍ ህግ መሰረት መከናወን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ኢትዮጵያና ግብፅ ከፈለጉ ሁለቱን አካላት በሮም ለማደራደርና ለማወያየት ፈቃደኛ ነን›› ብለዋል፡፡
በድርድር መፍትሄ የሚገኝበትን መንገድ ለማመቻቸትና ለማገዝም መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ጣሊያን የውሀ ጉዳይ ለግብፃዊያን ያለውን ጠቀሜታ እንደምትረዳ የጠቀሱት ታጃኒ በአለም አቀፍ ህግና በድርድር የውሀ ድርሻዋን እንድታገኝ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡ አክለውም የሮም መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ካለው ረጅም አመታት የዘለቀ ወዳጅነት የተነሳ ድርድሩን ማስጀመር እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

1 month ago