(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ በአንድ ቬንዙዌላዊ ስደተኛ ላይ ጥይት የተኮሰው የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ አስከባሪ ኦፊሰር የሆነው ክርስቲያን ካስትሮ፣ "ለምርመራ ቡድኑ የሐሰት ቃል ሰጥተሃል" በሚል ክስ ትላንት ሐሙስ አመሻሹ ላይ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ። የፌደራል ታላቁ የህግ ዳኞች ቡድን ባሳለፈው ረቡዕ ዕለት በካስትሮ ላይ ባለ ስድስት ነጥብ ክስ የመሰረተ ሲሆን፣ ግለሰቡ ቴክሳስ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ዛሬ አርብ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል።
ይህ ጉዳይ መጀመሪያ ላይ በሚኒሶታ የሄኔፒን ካውንቲ አቃቤ ህግ ቢሮ በኩል ክስ ተመስርቶበት የነበረ ቢሆንም፣ የቴክሳስ ገዥ የሆኑት ግሬግ አቦት ተከሳሹን አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የህግ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ካስትሮ ባለፈው ሳምንት ከቴክሳስ እስር ቤት በዋስ ተለቆ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ የፌደራል ክስ ሆኖ በመምጣቱ ዳግም ሊታሰር ችሏል።
የጥቃቱ ክስተት የተፈጠረው በትራምፕ አስተዳደር ዘመን የኢሚግሬሽን ክትትል እጅግ በጠበቀበት ወቅት ነበር። በጥር ወር ላይ ሁለት ስደተኞች (አልፍሬዶ አልጆርና እና ጁሊዮ ሴዛር ሶሳ-ሴሊስ) የፌደራል ፖሊሶችን አጥቅታችኋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው የነበረ ሲሆን፣ ሶሳ-ሴሊስ የተባለው ቬንዙዌላዊ ስደተኛ በዚሁ የኢሚግሬሽን ኦፊሰር እግሩ ላይ በጥይት ተመቶ ነበር።
መጀመሪያ ላይ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ፣ "ስደተኞቹ በትራፊክ ፍተሻ ወቅት ለማምለጥ ሞክረው ተጋጩ፣ ከዚያም በመጥረጊያ እና በአካፋ ፖሊሱን ሲያጠቁ ፖሊሱ ራሱን ለመከላከል ሲል ተኮሰ" የሚል መረጃ አውጥቶ ነበር። ነገር ግን በኋላ ላይ የወጡ የሞባይል ቪዲዮ መረጃዎች እና የኤፍቢአይ ምርመራዎች፣ ኦፊሰሩ የሰጠው ቃል ሐሰት መሆኑን አጋለጡ። ቪዲዮው እንደሚያሳየው ስደተኛው ቤቱ በር ላይ እንደደረሰ በቤተሰቡ ፊት በፖሊሶቹ ጥቃት ደርሶበታል።
ይህንን የቪዲዮ ማስረጃ ተከትሎ፣ በየካቲት ወር ላይ በስደተኞቹ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ የተደረገ ሲሆን፣ የኢሚግሬሽን ተጠባባቂ ኃላፊ የሆኑት ቶድ ላየንስ፣ "ካስትሮ እና ሌላ ተጨማሪ ኦፊሰር በፍርድ ቤት የሰጡት ቃል ሐሰት መሆኑ በቪዲዮ ተረጋግጧል" በማለት ሁለቱንም ከስራ አግደዋቸዋል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ፣ ካስትሮ ላይ የሲቪል መብት ጥሰት ክስ እንዳይመሰረትበት ከፍተኛ ጫና እንደነበር የተቃወሙት የፌደራል አቃቤ ህግ ማቲው ኢቫንስ ከስራ የተባረሩ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ሚስጥራዊ የውስጥ ኢሜል መረጃን አውጥተሃል በሚል በፍትህ ዲፓርትመንት ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተዘግቧል።

1 month ago