(ዘ-ሐበሻ ዜና) በዩናይትድ ስቴትስ ሚኒሶታ ግዛት ሴንት ፖል ከተማ ውስጥ የምትኖር አንዲት የ33 ዓመት ወጣት ኢትዮጵያዊት እናት መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ህይወቷ አልፎ የተገኘ ሲሆን፣ አብሯት የነበረው የሁለት ዓመት ህጻን ልጇ ከቀናት በኋላ ተአምራዊ በሆነ ሁኔታ በህይወት መገኘቱ ተገለጸ።
ፖሊስ ቤቱን ሰብሮ በገባበት ወቅት፣ አዱት (ፍጹም) ሳይመን ማልዋል የተባለችው እናት ህይወቷ አልፎ የተገኘች ሲሆን፣ ህጻኑ እናቱ ካረፈች ከሁለት ወይም ሶስት ቀናት ገደማ በኋላ በከፍተኛ የረሃብ እና የውሃ ጥም ድካም ውስጥ ሆኖ ተገኝቷል። ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ የህክምና ክትትል የተደረገለት ይህ ህጻን፣ በአሁኑ ወቅት ጤንነቱ በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ እና ለጊዜው ከሟች የክርስትና እናት ጋር እንደተቀላቀለ ታውቋል።
በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ደምስ ከበደ ስለ አደጋው ለሚዲያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ደምስ እንዳስረዱት፣ የሟች አስከሬን በራምዚ ካውንቲ የህክምና መርማሪ ቢሮ ምርመራ የተደረገበት ሲሆን፣ አሟሟቷም ከማንኛውም የሶስተኛ ወገን ጥቃት ነጻ የሆነ "ተፈጥሯዊ ሞት" (Natural Death) መሆኑ ተረጋግጧል።
"ልጁ መጀመሪያ ሲገኝ እጅግ በጣም ደክሞ ነበር፤ አሁን ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ በራሱ ይጫወታል፣ ይራመዳል" ሲሉ አቶ ደምስ የህጻኑን ሁኔታ ገልጸዋል። አክለውም ከሌላ ግዛት የመጣው የልጁ አባት በስፍራው ተገኝቶ ልጁን ከጠየቀ በኋላ ለቀብር ስነ-ስርዓቱ እንደሚመለስ ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ ከራምዚ ካውንቲ ጋር በመተባበር የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪዎችን ማመቻቸቱን የገለጹት ተወካዩ፣ በአሁኑ ሰዓት አስከሬኗ በቀብር አስፈጻሚ ተቋም ጥበቃ ስር እንደሚገኝ ተናግረዋል። የቀብር ስነ-ስርዓቱን ለማስፈጸምም ካልጋሪ፣ ካናዳ የምትኖረው የሟች እናት የጉዞ ሰነድ አግኝታ እስክትመጣ ድረስ እየተጠበቀ ይገኛል።
ይህን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ የሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ቤተሰቡን ለማገዝ እና ለቀብር ማስፈጸሚያ የሚሆን ድጋፍ እያስተባበረ መሆኑን አስታውቆ፣ በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ማህበረሰቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል።

1 month ago