የፊታውራሪ አመዴ ለማ ታሪክ በድምፅ ትረካ ሊቀርብ ነው
#ethiopia | አገራቸውን በልዩ ልዩ መንገድ ያገለገሉት ፊታውራሪ አመዴ ለማ የፃፉት የሕይወት ታሪክ መፅሀፍ በተወዳጅ ሚድያ አማካይነት በድምፅ ሊተረክ ነው፡፡
"የሕይወት ታሪኬ" በሚል ርዕስ የዛሬ 14 ዐመት መፅሐፍ ያሳተሙት ፊታውራሪ አመዴ ከልጅነት እስከ አዛውንትነት ዕድሜያቸው ለሀገር የሚጠቅም ተግባር በማከናወን ያለፉ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡
ይህን የሀገር አበርክቷቸውን፣በመፅሐፋቸው ላይ ግልፅ በሆነ መልኩ ያስቀመጡ ሲሆን በድምፅ ትረካ ሲቀርብም ለብዙዎች ተደራሽ እንደሚሆን ይገመታል፡፡
የድምፅ ትረካው በጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ የተተረከ ሲሆን ከፊታውራሪ አመዴ ለማ ቤተሰቦች ጋርም በትብብር የተዘጋጀ ቅንብር ነው፡፡
የአክሱም ሀውልት መመለስ ላይ ፊታውራሪ አመዴ ለማ ትልቅ ሚና የነበራቸው ሲሆን የታሪክ፣ የባህልና የንግድ ዕውቀታቸው ብስለትን የተላበሰ ነው፡፡
እርሳቸው የሦስቱን መንግስታት ዘመን በደንብ ያውቁ ስለነበር ከዚያ ቀደም የአክሱም ሀውልትን ለማስመለስ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አብጠርጥረው ይረዱ ነበር።
በ1948 ዓ.ም በህዝብ ጥቆማ በጃንሆይ የፓርላማ አባል በመሆን በቅንነት እና በታማኝነት ያገለገሉት ፊታውራሪ የሕዝብን ጥያቄ ያለ ፍርሀት በማንሳት የተከበሩ ነበሩ፡፡
.
ፊታውራሪ አመዴ ለማ፣ ከንጉሡ እስከ ኢሕአዴግ ባሉት መንግስታት ውስጥ የተመለከቷቸውን ጥሩ ነገሮች ማድነቅ እንደሚችሉት ሁሉ ያላመኑበትንም ትህትና በታከለበት ግልጽነትና በድፍረት በመናገር ይታወቃሉ፡፡ ለዚህ ማስረጃ በንጉሡ ዘመን ለተለያዩ አካላት የፃፏቸው ደብዳቤዎች ናቸው፡፡
ፊታውራሪ አመዴ ለማ የአክሱም ሀውልት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአክሱም ስልጣኔ ማሳያ የሆኑ ቅርሳ ቅርሶች እንዲመለሱ ያደረጉት ጥረት በሙሉ የተሳካ ነበር። የእስልምና ሀይማኖት አባት ቢሆኑም በጣልያን መንግስት ለተዘረፉ የአብያተ-ክርስትያናት ቅርሶች ወገባቸውን ይዘው የዲፕሎማሲ ሥራቸውን አከናውነዋል፡፡
በ1908 ዓ.ም የተወለዱት ፊታውራሪ አመዴ ለማ (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2001 ዓ.ም.) በ89 ዓመታቸው አርፈዋል፣ በሞቱ ወቅት 10 ልጆች፣ 34 የልጅ ልጆች እና 6 የልጅ ልጅ ልጆችን አይተዋል፡፡
የእርሳቸውን የሕይወት ታሪክ የያዘው ተከታታይ ትረካ 20 ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን ከሰኔ 30 2017 በኃላ ከምሽቱ 3ሰዐት አንስቶ tewedajemedia tube ላይ መተረክ ይጀምራል፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን መፅሀፎችን ወደ ድምፅ መተረክ ከጀመረ 7ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት 30 በላይ መፅሐፎችን በትረካ ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህም መሐል የኤርትራ ጉዳይ፣የአሰብ ወደብ ሥራ፣ ማማ በሰማይ፣የሀይሌ ፊዳ ታሪክ፣ የዶክተር አክሊሉ ሀብቴ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ እና ሌሎችም መፅሐፎች ይገኙበታል፡፡https://youtube.com/tewed...

1 year ago