Logo
YenetaTube
በበጀት ዓመቱ የ7.5 ቢሊዮን ብር የቤት ሽያጭ ያከናወነው ጊፍት ሪል ስቴት ለአዲሱ ዓመት ልዩ የዋጋ ቅናሽ ይፋ አደረገ

ዘጋቢ፦ የኔታ ሚዲያ

ጊፍት ሪል ስቴት በ2018 በጀት ዓመት የዲጂታል ሚዲያ አማራጮችን እና የቀጥታ የገበያ ስልቶችን በመጠቀም ከ1,200 በላይ ለመኖሪያና ለንግድ የሚሆኑ ቤቶችን በመሸጥ ከ7.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስመዝገቡን አስታወቀ።

ድርጅቱ ያስመዘገበውን የስኬት ጉዞ ተከተሎ ለመጪው የ2019 አዲስ ዓመት ደንበኞቹን የሚያበስሩ አዳዲስ የቅናሽ እና የክፍያ አማራጮችን ይፋ አድርጓል።

በጥቅሉ በቀረቡት አዳዲስ የሽያጭ ዕቅዶች መሰረት በቦሌ አትላስ፣ በቦሌ መድኃኔዓለም፣ በፊጋ እንዲሁም በሌሎች የልማት ሳይቶች የሚገነቡ ቤቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

እንደየሳይቶቹ የግንባታ ደረጃ ከ2 እስከ 15 በመቶ ቅድመ ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች ከ5.5 እስከ 10 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ የሚደረግ ሲሆን፤ ከ35 እስከ 100 በመቶ የሚሆኑ ክፍያዎችን አስቀድመው ለሚያጠናቅቁ ደግሞ ከ8 እስከ 18 በመቶ ቅናሽ ተዘጋጅቷል።

በተጨማሪም ሙሉ ክፍያ (100 በመቶ) በቅድሚያ የሚፈጽሙ ደንበኞች ወደፊት ከሚከሰት ማንኛውም የዋጋ ጭማሪ ነፃ እንደሚሆኑ ድርጅቱ አረጋግጧል።

በሌላ በኩል ደንበኞች የቤቱን ዋጋ 55 በመቶ በራሳቸው ሲሸፍኑ ቀሪውን 45 በመቶ በባንክ ብድር የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ የተመቻቸ ሲሆን፣ የግንባታ ደረጃቸው 95 በመቶ ለደረሱ ብሎኮች ደግሞ 25 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመክፈል ቀሪውን በሂደት መክፈል የሚያስችል አማራጭ ቀርቧል።

ይህ ለአዲሱ ዓመት የተዘጋጀው ልዩ የቅናሽ እና የክፍያ ማቃለያ ዕድል ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ጊፍት ሪል ስቴት አስታውቋል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.