Logo
SeledaPost
ተሽከርካሪዎች የለጠፉትን ጥቁር ስቲከር እንዲያነሱ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ አሳሰበ
****

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተለዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ወይም VIP ተሽከርካሪዎች በስተቀር ከዛሬ  ማክሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ከተማ ፣ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ ማናቸውም ተሽከርካሪዎች መስታወት ላይ የተደረጉ ጥቁር ስትኬሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነቀሉ ማሳሰቢያ ሰጠ።

ኮሚሽኑ በክልሉ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ እንዲሁም የጸጥታ ቁጥጥር ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ፣ የግል ፣ የንግድ ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች በሙሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ይህ የጸጥታ መመሪያ በሁሉም የክልሉ አወቃቀሮች በጥብቅ የሚተገበር ሲሆን፤ መመሪያውን ጥሰው በተሽከርካሪዎቻቸው መስታወት ላይ ጥቁር ስትኬር ይዘው በተገኙ አካላት ላይ ኮሚሽኑ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝቧል።

የመንግሥት አመራሮች፣ ሕብረተሰቡና የድርጅት ኃላፊዎች ለሕግ ማስከበር ሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.