(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ሴናተር በርኒ ሳንደርስ የእስራኤልን ወታደራዊ ፖሊሲዎች እና በዌስት ባንክ (ምዕራብ ዳርቻ) የሚገኙ ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ እያደረሱ ያለውን ጥቃት በጽኑ አውግዘዋል። ሴናተሩ ይህንን ቁጣቸውን የገለጹት፣ ጡረታ የወጡ የእስራኤል የጦር ጀነራሎች የሰጡትን አስደንጋጭ ምስክርነት የሚያትተውን የ'ኒውዮርክ ታይምስ' ዘገባ በ'ኤክስ' ገጻቸው ላይ በማጋራት ነው።
ሳንደርስ በመልዕክታቸው "በዌስት ባንክ ፍልስጤማውያንን እያሸበሩ ያሉትን የእስራኤል ሰፋሪዎች ድርጊት የሚቃወሙትን ጡረተኛ የእስራኤል ጀነራሎች ንግግር አድምጡ" ሲሉ አሳስበዋል። በዘገባው ላይ ከተጠቀሱት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መካከል፣ የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና ጡረተኛው ብርጋዴር ጀነራል ኤፍሬም ስኔህ፣ ሰፋሪዎቹ እያደረሱ ያሉትን ጥቃት "ይህ የዘር ማጽዳት ወንጀል ነው" ሲሉ በግልጽ ኮንነውታል።
በተጨማሪም ሌላኛው ጡረተኛ የአየር ሀይል ጀነራል አሳፍ አግሞን "አንድ ማህበረሰብ በዚህ መልኩ አሰቃቂ ድርጊት መፈጸም ከጀመረ፣ ያ ማህበረሰብ በእርግጠኝነት የጠፋ ነው" ሲሉ የሁኔታውን አሳሳቢነት አስጠንቅቀዋል።
ሴናተር በርኒ ሳንደርስ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጥብቀው እንደሚቃወሙ በድጋሚ በማረጋገጥ፣ "ለአክራሪው የኔታንያሁ መንግስት ከዚህ በኋላ አንዲት ሳንቲም አንሰጥም!" ሲሉ ጽኑ አቋማቸውን አሳውቀዋል።

1 month ago