Logo
SeledaPost
:-«ቅጠል እየበላን ነው»‼️ — በወለጋ የተፈናቃዮች የረሃብ አደጋ እና አዲስ የታጣቂዎች ጥቃት‼️
👉ጥቃቱ የአማራ ብሄር ተወላጅ በተባሉት ላይ ያነጣጠረ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ «አሊ» ጫካ ውስጥ የተጠለሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በከባድ ረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው እያለፈ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ «አሊ» በተባለ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ላለፉት 15 ቀናት ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች በምግብ እጥረትና በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው እያለፈ እንደሚገኝ ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ጠቆሙ።

ወደ ስፍራው የሚወስዱ መንገዶች በመዘጋታቸውና ገበያዎች በመቃጠላቸው ተፈናቃዮቹ ላለፉት 15 ቀናት በክረምት የበቀሉ ሳርና ቅጠላቅጠሎችን እየተመገቡ ለመቆየት መገደዳቸውን መረጃ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ወደ አካባቢው የሚወስዱ መንገዶች በመዘጋታቸው፣ የመኖሪያ ቤቶችና የምግብ አቅርቦት ይገኝባቸው የነበሩ አቅራቢያ ገበያዎችና መንደሮች ሙሉ በሙሉ በመቃጠላቸው ምክንያት በርካታ እናቶች፣ ሕፃናትና አዛውንቶች ያለ ምንም የሰብአዊ እርዳታ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮቹ ላለፉት ቀናት በክረምት የበቀሉ ሳርና ቅጠላቅጠሎችን እየተመገቡ ለመቆየት መገደዳቸውንና በአሁኑ ወቅት ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱን አስታውቀዋል።

በዛሬው ዕለት ብቻ በረሃብ ምክንያት የሁለት ሕፃናትና የአንድ አዛውንት ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል::

አስቸኳይ እርዳታ ካልቀረበ የብዙዎች ሕይወት ሊያልፍ እንደሚችል ተጠቁሟል::

በአሊ ጫካ ውስጥ የተጠለሉት ተፈናቃዮች እንደሚገልጹት አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ካልቀረበ በሚቀጥሉት እስከ 2,000 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ የሚችልበት ከፍተኛ ስጋት አለ።

በተመሳሳይ በቄለም ወለጋ ዞን ሀዊ ገላ ወረዳ «መንደር 17» ዛሬ ማለዳ ታጣቂዎች በአማራ መኖሪያ መንደሮች ላይ አዲስ ጥቃት ከፍተዋል፡፡

ዛሬ ማለዳ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ወደ መንደር 17 ዘልቀው በመግባት ጥቃት የከፈቱ ሲሆን፣ ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ ማርፈዱ ተገልጿል።
በጥቃቱ ሳቢያ የደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት መጠን እስካሁን በውል ያልታወቀ ሲሆን፣ በአካባቢው ከፍተኛ ፍርሃት እና ውጥረት ነግሦ ይገኛል ተብሏል ።                 

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.