(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትራምፕ አስተዳደር ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ብቻ ከአፍጋኒስታን፣ ኩባ፣ ኒካራጓ እና ሌሎችም ሀገራት የመጡ ከ100 በላይ ስደተኞችን ምንም ዓይነት ትስስር ወደሌላቸው ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ማባረሩን ሲቢኤስ ኒውስ አጋለጠ።
የመንግስት የውስጥ ሰነዶችን ዋቢ አድርጎ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ስደተኞቹ በሶስት ዙር በረራዎች ወደ ቡሩንዲ፣ ካሜሩን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤስዋቲኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሩዋንዳ እና ሴራሊዮን ተልከዋል። ተባራሪዎቹ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ምንም አይነት የዜግነትም ሆነ ሌላ ትስስር የሌላቸው ሲሆኑ፣ እርምጃው አስተዳደሩ ስደተኞችን ወደ "ሶስተኛ ሀገር" ለመላክ የጀመረው ስምምነት አካል ነው።
ይሁን እንጂ ስደተኞቹ ከተላኩባቸው ሀገራት መካከል እንደ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ያሉት በእርስ በርስ ግጭት የሚታመሱ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ ፈጽሞ እንዳይጓዙባቸው ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ (Level 4) የሰጠባቸው አደገኛ አካባቢዎች መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) በጉዳዩ ላይ በሰጠው ምላሽ፣ "ሕገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ፣ በሕጉ መሠረት ሌላ ደህንነቷ የተጠበቀ ሀገር መፈለግ ግዴታችን ነው። ነገር ግን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከመረጡ ነፃ የበረራ ትኬት እና የ3,000 ዶላር ቼክ እንሰጣቸዋለን፤ ምርጫው የራሳቸው ነው" ብሏል። አብዛኞቹ ተባራሪዎች ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው ወደ አሜሪካ ከመግባታቸው ውጭ ምንም ዓይነት የወንጀል ሪከርድ የሌላቸው መሆናቸው በሰነዱ ተጠቅሷል።

1 month ago