Logo
FastMereja
ለአየር ንብረት መዛባት ጸሎትና ምልጃ ተካሄደ

በጌዴኦ ዞን እና በሀገራችን የተከሰተውን የአየር ንብረት መዛባት ተከትሎ፤ በገደብ ወረዳ የሚገኙ የባህላዊ ሃይማኖት አባቶች (የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የባህል መሪዎች) ጸሎትና ምልጃ አካሂደዋል።

አባቶቹ በአካባቢው ባህልና ትውፊት መሠረት ፈጣሪ ዝናብ እንዲሰጥ ሰላም እንዲያወርድ እና ህዝቡን ከተፈጥሮ አደጋ እንዲጠብቅ ተማጽነዋል።

ይህ የባህላዊ ሃይማኖት አባቶች ጸሎት፤የዞኑ ሃይማኖት ተቋማት ካወጁት የ3 ቀናት የጸሎት መርሃ-ግብር ጋር ተዳምሮ መላው ማህበረሰብ ችግሩን በእምነትና በአንድነት ለመሻገር እያደረገ ያለውን ጥረት የሚያሳይ መሆኑን ዳራሮ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ያገኘው ዘገባ ያመላክታል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.