ቶተንሃም ሆትስፐር ሁለተኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳውና በደጋፊው ፊት በኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አንቶኒ ኤላንጋ እና ዊሳ አስቆጥረዋል፡፡
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ትላልቅ ዝውውሮችን በመፈጸም ክዋክብትን የግሉ ያደረገው የሮቤርቶ ዲ ዘርቢው ቶተንሃም በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት በተደረገው የሊጉ የመክፍቻ ጨዋታ በብሬንፎርድ 3 ለ 0 መሸነፉ አይዘነጋም፡፡
ዛሬ ቀደም ብለው በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም እንዲሁም ቦርንማውዝ ከኤቨርተን አቻ የተለያዩ ሲሆን፤ ሃል ሲቲ ኮቨንትሪ ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

1 month ago