Logo
Getu Temesgen
🇪🇹 በኬንያ ደምቀው ያበሩት የነገ ተስፋዎች ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ🏆

🇪🇹በቦሌ ኤርፖርት አቀባበል ይደረግላቸዋል
#ethiopia | ከሠባት አመታት መቋረጥ በኋላ በኬንያ አስተናጋጅነት በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ሁለተኛው የANOCA ዞን 5 የወጣቶች ጨዋታዎች (ANOCA Zone V Youth Games) ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ወጣት ኦሎምፒያን ቡድን በውድድሩ በ12 ሜዳልያ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

በውድድሩ ሴድስት ወርቅ፣አራት ብርና ሁለት የነሐስ ሜዳልያ ያገኘው የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ቡድን በኬንያ የነበረውን የሁለት ቀናት ቆይታ አጠናቆ ዛሬ ምሽት 1:30 አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለልዑካን ቡድኑ በኤርፖርት የእንኳን ደህና መጣችሁ የጀግና አቀባበል እንደሚደረግላቸው ያገኘነው ዜና ይጠቁማል።

በቀጣይ በማርዮት አሊያም በሌላ በተመረጠ ስነ-ስርዓት ሜዳልያ በማምጣት የሀገራቸውን ስም ላስጠሩ ወጣት አትሌቶችና ተሳታፊዎች እንዲሁም የልዑኳን ቡድን እንደየተሳትፎአቸውና ውጤታቸው ኦሎምፒክ ኮሚቴው ለሽልማት እጁን እንደሚዘረጋ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

የዘንድሮውን ውድድር በብዙ ስፖርቶች የተሳተፈችው ኬንያ በአጠቃላይ 51 ሜዳልያ ከዘጠኝ ሀገራት በበላይነት ስታጠናቅቅ ኡጋንዳ ደግሞ በ23 አጠቃላይ ሜዳልያ ሁለተኛ፣ኢትዮጵያ በ12 ሜዳልያ በሶስተኛነት አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ወጣት ኦሎምፒያን ያስመዘገቡት ውጤት በቀጣይ ኦክቶበር 31 በሴኔጋል ዳካር በሚደረገው የአለም ወጣቶች ኦሎምፒክ የተሻለ ተሳትፎና ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ በሚል ከወዲሁ ተስፋ ተደርጎባቸዋል።

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.