"ሰው እንጂ ሀገር ያረጃል ብለን አናስብም ነበር" - በቁጭትና በእንባ የታጀበው የአሰብ ልጆች ትዝታ
*******************
በአንድ ወቅት የቀይ ባህር ሞገድ ከአሰብ የወደብ ጠረፍ ጋር ሲላተም የሚፈጥረው ድምፅ ተራ የተፈጥሮ ዜማ አልነበረም፤ የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት የልብ ምት እንጂ።
የሙስሊሙና የክርስቲያኑ ህዝብ በፍቅር፣ በመቻቻልና በይቅርታ የሚኖርባት የቀድሞዋ የወደብ ከተማ አሰብ ዛሬም በልባቸው ውስጥ እንደማይጠፋ የብርሃን ፈርጥ ሆና ትኖራለች።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቀድሞ የአሰብ ከተማ ነዋሪዎች 1ሺህ 501ኛውን የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓልን በጋራ ባከበሩበት ወቅት፣ ለአሰብ የወደብ ከተማ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅርና ትዝታ በስሜትና በለቅሶ አጋርተዋል።
የሙስሊሙና የክርስቲያኑ ማህበረሰብ በፍቅርና ተቻችሎ ይኖሩባት የነበረችው የአሰብ ከተማ፣ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር በተከፈተበት ወቅት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር የሚያስታውሱት ማህበርተኞቹ፤ ከተማዋ አርጅታና ተጎሳቁላ በማየታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ከኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ጋር ቆይታ ያደረጉት እነዚህ የአሰብ ቤተሰቦች፣ ቀደም ሲል የነበሩት የነዳጅ ማጣሪያ፣ የጨው ማውጫ ቦታዎችና ሌሎች ልዩ ትዝታ ያላቸው ስፍራዎች መልካቸውን ቀይረው ወደ ኋላ ቀርተው ማየታቸውን ተናግረዋል።
አሰብ የነበረው የነዳጅ ማጣሪያ የነበረውን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ዘግይተው እንደተረዱት የሚያነሱት እነዚህ ቤተሰቦች፤ "ሰው እንጂ ሀገር ያረጃል ብለን አናስብም ነበር፤ አሁን ግን አሰብ አርጅታና ተጎስቅላ ተመልከተናል" ሲሉ በቁጭት ያስታውሳሉ።
የአሰብ ልጆች በተለያዩ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ተፈላልገውና ተገናኝተው የራሳቸውን ማህበር መስርተዋል። የማህበሩ አስተባባሪ አቶ ሀጎስ እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል የማህበሩ አባላት ይገናኙ የነበረው በችግርና በለቅሶ ጊዜ ብቻ ነበር ይላሉ።
በአንድ ወቅት የአንድ ወንድማቸውን ህልፈት ተከተሎ በተካሄደ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ከ700 በላይ የአሰብ ልጆች በአንድ ላይ ተገኙ። በወቅቱ ለ20 እና ለ30 ዓመታት በህይወት የሉም ተብለው ተስፋ የተቆረጠባቸው የድሮ ጓደኞች በመገናኘታቸው፣ ሁልጊዜ በለቅሶ ብቻ ከመገናኘት ይልቅ በደስታና በችግር ጊዜ የሚረዳዳ ማህበር የመስረት ሀሳብ ተወለደ።
በዚህም መሰረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አካባቢ «ተስፋ ለአሰብ መረዳጃ እድር» በሚል ህጋዊ እውቅና አግኝተው በጋራ መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
አሰብ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ማህበረሰብ መካከል ባለው ጠንካራ ፍቅርና መከባበር የምትታወቅ ነበረች። ወይዘሮ ከድጃ የተባሉ የቀድሞ አሰብ ከተማ ነዋሪ ትዝታቸውን በእንባ እየተራጩ እንደተናገሩት፣ በከተማዋ የሃይማኖትም ሆነ የብሔር ልዩነት አይታወቅም ነበር። የክርስትና በዓል ሲሆን ሙስሊሙ፣ የሙስሊም በዓል ሲሆን ደግሞ ክርስቲያኑ አብሮ ያከብራል። በመውሊድና በጥምቀት በዓላት ወቅት ሰራተኛው ከልብ ተነሳስቶ ገንዘብ በማዋጣትና በጉልበቱ በማገልገል በጋራ ያደምቅ ነበር ይላሉ ።
የብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ግብ ጠባቂ የነበረው ጥላሁን እሸቱ (ጥላሁን ጆርጅ) እና ሌሎች የማህበሩ አባላትም የነበራቸውን የልጅነት ትዝታ አጋርተዋል። የኬሚስትሪ መምህርት የሆኑት ሌላኛው የማህበሩ አባል በበኩላቸው፣ የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የነበረውን ትልቅ ፋይዳ አሁን ላይ በደንብ እንደሚረዱት ገልጸው፣ ከተማዋ ወደ ነበረችበት ልማትና እድገት እንድትመለስ ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።
የኢትዮ-ኤርትራ ሰላም ከወረደ በኋላ የማህበሩ አባላት ወደ አሰብ ባደረጉት ጉዞ፣ በቦታው የሚገኙ ኤርትራውያን ወንድሞቻቸው እስከ "አይሞከር" ስፍራ ድረስ መጥተው በእንባና በመዝሙር እንደተቀበሏቸው ያስታውሳሉ።
የማህበሩ አባላትም ለሁለት መስጊዶችና ለሁለት ቤተክርስቲያናት የሚሆኑ አጠቃላይ የ800 ሺህ ብር ቁሳቁሶችን እኩል በመመደብ ገዝተው በስጦታ አበርክተዋል።
በመጨረሻም የማህበሩ አባላት፣ ይህ የፍቅርና የአብሮነት ባህል ለልጆቻቸውም እንዲተላለፍ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸው፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የሃይማኖቱ ተከተዮችና ለአሰብ ልጆች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን አስተላፍለዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ

2 months ago