የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የስራ ዘመናቸውን በ2027 እንደሚያጠናቅቁ አስታወቁ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመጪው የፈረንጆቹ ነሐሴ 2027 የስራ ዘመናቸውን እንደሚያጠናቅቁ ይፋ አደረጉ።
ዋና ዳይሬክተሩ አፍሪካ የራሷን የጤና አጀንዳ በባለቤትነት መምራት እንዳለባትና የውጭ ጥገኝነትን በማስቀረት ራሷን መቻል እንደምትችል ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተጀመረው የድርጅቱ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በቪዲዮ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ኃላፊነታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት ይህ በዋና ዳይሬክተርነት የተገኙበት የመጨረሻው የቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በ2017 በዚምባብዌ ባደረጉት ንግግር አባል ሀገራት የየራሳቸውን የጤና አጀንዳ በመሪነት መያዝ አለባቸው ማለታቸውን ያስታወሱት ዶ/ር ቴድሮስ አሁን ላይ ይህ ሀሳብ አፍሪካ የራሷን ጤና በፋይናንስ የምትደግፍበት ፣ የምታስተዳድርበት እና የምታቀርብበት መሰረታዊ መርህ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
አህጉሪቱ አሁን ላይ ወሳኝ በሆነ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ዶ/ር ቴድሮስ አፍሪካ ከምታገኘው የውጭ እርዳታ ይልቅ በገንዘብ ዝውውር እና በከፍተኛ የዕዳ ክፍያ ምክንያት የምታጣው ሀብት በእጅጉ እንደሚበልጥ ጠቁመዋል።
የጤና ታክሶችን በአግባቡ በመጠቀም አፍሪካ የህዝቧን ጤና በራሷ አቅም መደገፍ እንደምትችል ዶ/ር ቴድሮስ በንግግራቸው ገልጸዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ ሁላችንም በጋራ የምንፈልጋትን ጤናማ ፣ ደህንነቷ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የሆነች አፍሪካ መገንባት አለብን ብለዋል።
በተጨማሪም አባል ሀገራት በመጪው ግንቦት በሚካሄደው የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ የድርጅቱን ዘላቂ የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ የሚደረገውን የመዋጮ ጭማሪ እንዲያጸድቁ ዶ/ር ቴድሮስ ጠይቀዋል።
ሀገራቱ ከዓለም አቀፍ የጤና መዋቅር ማሻሻያ ጋር በንቃት እንዲሳተፉ ፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ እየተደረገ ያለውን ምላሽ እንዲደግፉና ድርጅቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ የሚሰራውን ስራ እንዲያግዙ አሳስበዋል።
በመጨረሻም "የእናንተ ዋና ዳይሬክተር ሆኜ ማገልገል በሕይወቴ ትልቁ ክብር ነው" ሲሉ የተናገሩት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን እስከሚያስረክቡ ድረስ በቀሪው አንድ ዓመት ላስቀመጡት ራዕይ አባል ሀገራቱና የድርጅቱ ባልደረቦች ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በፋሲል አረጋይ

2 months ago