Logo
SeledaPost
የገዱ አንዳርጋቸው ንጹህ እንጀራ ።

ከመሸ ፌስቡክ ላይ የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ኋላ ላይም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፡ በሀገረ አሜሪካን የፓርኪንግ ስራ ሲሰሩ የሚያሳይ ቪዲዮ አየሁ ።
........
አደለም የአንድ ክልል ፕሬዝደንት ፡ አደለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረ ሰው ይቅርና ፡ ተራ የገቢዎችና ጉምሩክ ሰራተኛ እንዲሁም በተለያየ የመንግስት ቢሮዎች ያሉ ሃላፊዎች  ዱባይ ውስጥ ቪላ በሚገዙበት ዘመን ።

ተራ ባለስልጣን በዘመድ አዝማዱ ስም ሚሊዮኖችን በባንክ በሚያስቀምጥበት ጊዜ ፡
የሀገርን ሀብት በውጭ ባንኮች የሚያስቀምጡ እልፍ ባለስልጣኖች ባየንበት ዘመን ፡ ልጆቻቸውን በአውሮፓና አሜሪካ የሚያስተምሩ ሙሰኞች በሞሉበት ጊዜ ፡ ደጉ አንዳርጋቸው የሚባል ሰው ፓርኪንግ እየሰራ ይገኛል ሲባል የማይገረም ማን ይኖራል  ?
.....
አቶ ገዱ ስለሚያራምደው ፓለቲካዊ አመለካከትም ሆነ ሌላ ነገር  ግድ የለኝም ። በስልጣን በነበረበት ጊዜ  ከዚች ድሀ ሀገር ሳይዘርፍ በመኖሩ ግን በአክብሮት እጅ ለመንሳት እገደዳለሁ ። ማንም ሰው ይህን አለማድነቅ አይችልም ።
አቶ ገዱ  ቢፈልግኮ ይህኔ በአሜሪካን ባንኮች መቶ ሚሊዮኖችን ማስቀመጥ ይችል ነበር ። ሆኖም አላደረገውምና ዛሬ ላይ ፓርኪንግ ተቀጥሮ እየሰራ የሰላም እንቅልፍ ተኝቶ ያድራል ።
....
የገዱ ንፁህ እንጀራ ያስቀናል ፡ በሙስና ያልቆሸሸ ፡ ከድሃ ሀገር ከተዘረፈ ገንዘብ ጋር ያልተነካካ ንፁህ እንጀራ ።

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.