ኢትዮጵያ ለመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ፍትህን በመስጠቷ በወርቅ ቀለም የተጻፈው ታሪኳ ዛሬም በመውሊድ በዓል አከባበር ደምቆ ይታያል
********************
የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል (መውሊድ) መንፈሳዊ ምጥቀቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በጋራ የኖርንበትን የይቅርታ፣ የአብሮነትና የሰላም እሴት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር የምናሳይበት ታላቅ መድረክ ነው። ቂምን በይቅርታ በማበስ ሰላምን ማስፈን የበዓሉ መንፈሳዊ ምሶሶ ነው።
“የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ታሪክ ትውልድን በበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው” የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የነቢዩን ሕይወትና ገድል መሠረት በማድረግ ትውልድን በበጎ እሴቶች ማነጽ እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ።
እነዚህ እሴቶች በኢትዮጵያ ምድር በተጨባጭ ካለው የማኅበረሰብ አብሮነት ጋር በጥልቀት የተሳሰሩ በመሆናቸው፣ በየመንደሩ የሚዘረጋው የመውሊድ ማዕድ ከህፃናት እስከ አረጋውያን፣ ከችግረኞች እስከ እንግዶች ሁሉም እኩል የሚቋደሱት የጋራ ደስታ መገለጫ ነው።
አቅም ለሌላቸው አጋርነትን ለማሳየት ጭምር የሚከናወነው ይህ ሰናይ ተግባር፣ የማኅበረሰብን የጋራ ደህንነትና ሥነልቦናዊ አንድነት ያጠናክራል።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያዎቹ ሙስሊም ስደተኞች የደህንነት ከለላ እና ፍትህን በመስጠቷ በወርቅ ቀለም የተጻፈው ታሪኳ ዛሬም በመውሊድ በዓል አከባበር ደምቆ ይታያል።
ለልዩነቶች እውቅና በመስጠት በአንድነት አብሮ የመኖር ጥበባችን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ባህሎች፣ ሃይማኖቶችና ማንነቶች የመቻቻል ማዕከል አድርጓታል።
መውሊድ የነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ድንቅ የሰላም፣ የይቅርታ እና የፍቅር አስተምህሮ በመዘከር በበጎ ታሪክ ትውልድን የምንቀርጽበት፣ ማዕድ በመጋራት ፍቅርን የምንዘራበት እንዲሁም ሀገራዊ ሰላም እና አንድነታችንን የምናጠናክርበት ታላቅ በዓል ነው።
በነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) አስተምህሮ የሚሰበከው የሰላም፣ የይቅርታ እና የፍቅር እሴት ከኢትዮጵያውያን የቆየ የመቻቻል ባህል ጋር ተዋህዶ ለቀጣናው እና ለመላው አፍሪካ ተምሳሌት ሆኖ ይቀጥላል።
መልካም የመውሊድ በዓል!
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #mawlid #prophetmuhammad #ebc

2 months ago