Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓ.ም (ዓመተ ምህረ) እኢአ ( እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ) እና ዓ.ል (ዓመተ ልደት ) እንዲባል ምክክሩ ተስማምተዋል

በኢትዮጵያ "የነገ ዕጠፋ ፋንታ" ሲሉ በጠሯቸው ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ የቆዩ ተመካካሪዎች አሁን ያለው የዘመን አቆጣጠር እንዲቀጥል በተጨማሪም ዓመተ ልደት፣እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር እና የሂጅራ የዘመን አቆጣጠር ቢካተት የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርበው ምክክሩ ተጠናቋል፡፡

ጉባዔተኛውም በዚሁ ሀሳብ ላይ ተስማምቷል፡፡

የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዓመተ ምህረት የሚለው "አካታች ስላልሆነ ይቅር" የሚል ምክር ሀሳብ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም እንዳይቀር ጉባዔተኞች ተስማምተው ነገር ግን ዓመት ልደት ፣እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የሚለው ስራ ላይ ቢውል ሲሉ ምክረ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም ዓመተ ሂጅራም ቢካተት በሚለው ላይ ተመካካሪዎች ተግባብተናል ብለው የምክረ ሀሳብ ሰነዱን አስረክበዋል፡፡

ተመካካሪዎች ሌላው የተስማሙባቸው ጉዳዮች የኢሬቻ በዓል እና የበዓለ 50 ባዓል በካላንደር ታስበው ይዋሉ በሚለው ነው፡፡

ለሙስሊሞች ጁማዓ የስግደት ሰዓት ከ5 እስከ 8 ሰዓት ይሁን በሚለው መስማማታቸውን የሚያስረዳው ለ4ሺ ጉባዔተኛ በንባባ የቀረበው ሰነድ ለ7ኛ ቀን አድቬንቲስት እምነት ተከታዮች እለተ ቅዳሜ አስገዳጅ የስራ እና የፈተና ቀን እንዳይሆንም መስማማታቸውን ያስረዳል፡፡

በዩኔስኮ የተመዘገቡ በዓላት ደግሞ "ህዝባዊ" በዓላት እንዲሆኑ መስማማታቸውን ይጠቅሳል፡፡

Via Sheger FM

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.