(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ኤርትራ ለመጀመሪያ ጊዜ ወክላ በሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር ላይ የምትሳተፈው ሞዴል ስኒት ሃብተአብ ከጋዜጠኛ ሳብሪና ሰለሞን "ያለፈችውን እናትሽን መታሰቢያ ለማክበር የጡት ካንሰር ግንዛቤን ለማስጨበጥ ባሉሽ መድረኮች ስትጠቀሚ ቆይተሻል። ይህን የግል የሐዘን ስሜት ወደ አደባባይ የማስተማር ሥራም ሆነ ማህበራዊ ንቅናቄ መቀየርሽ የራስሽን ውስጣዊ ጥንካሬ እና የሰብዓዊነት ሥራዎችሽን እንዴት ቀርጾታል?" ስትል ጠይቃት ነበር።
ስኒት ስትመልስ እንዲህ ብላለች፡ "እናቴን በሞት ማጣት እጅግ ከባድ ፈተና ነበር፤ ልክ ቤተሰቤ እህቴ 'ዳውን ሲንድረም' ንዳለባት ሲያውቅ ሁኔታውን ለመቀበል እንደተቸገረው ዓይነት ማለት ነው። ያም ሆኖ፣ የሕይወት እጅግ ፈታኝ ወቅቶች ብዙውን ጊዜ የመጨረሻውን የሕልውናችንን ግብ ፍንትው አድርገው እንደሚያሳዩን አምናለሁ። የእናቴን ትዝታ በልቤ ሰንቄ፣ የእህቴን መንከባከብ ኃላፊነት መረከቤ ለሕይወቴ አዲስና በዓላማ የተቃኘ አቅጣጫ ሰጥቶታል። በአሁኑ ጊዜ... ዋነኛ ተልእኮዬ ለእህቴም ሆነ ለእናቴ ድምፅ መሆን ነው።
"እናቴ አሁን በሕይወት ብትኖር ኖሮ፣ ሁሉም ሰው የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራን ቅድሚያ እንዲሰጠው ትወተውት ነበር። ምክንያቱም በሽታውን በጊዜ ማወቅ ሕይወትን ከማትረፉም በላይ፣ እናቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተጨማሪ ውድ ዓመታትን እንዲያሳልፉ ዕድል ይሰጣል። እኔም ይህንን የእርሷን መልእክት ተሸክሜ በመጓዝ፣ ሌሎች ሰዎች የገጠማቸውን መከራ በተለየ እና ገንቢ በሆነ መነጽር እንዲመለከቱት አበረታታለሁ። የምንጋፈጠው እያንዳንዱ ፈተና በእኛ ላይ የተጣለ አደራ ነው፤ ያንን የሐዘን ስብራትም ለሌሎች ትርጉም ወዳለው እና በጎ ወደሆነ ተግባር የመቀየር ሙሉ አቅም አለን።"

2 months ago