በአቶ ታዬ ደንደአ ላይ የተላለፈው የአራት ዓመት እስር ፍርድ በሰበር ሰሚ ችሎት ጸና
#fastmereja I የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ በፍርድ ቤት ተወስኖ የነበረውን የአራት ዓመታት እስር ፍርድ ሙሉ በሙሉ ማጸናቱን አስታወቀ።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአዲስ አበባ ባስቻለው ችሎት በቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ የቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን የአራት ዓመት ቅጣት አጽንቷል።
አቶ ታዬ በመጀመሪያ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት «ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት» በሚል በተመሠረተባቸው ክስ የሰባት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የነበረ ቢሆንም፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ቅጣቱ ወደ አራት ዓመት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር። ይሁን እንጂ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ የነበራቸው አቶ ታዬ፣ አምስት የመከራከሪያ ነጥቦችን በማንሳት ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ችሎቱ የቀረበውን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቷል።
የአቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት፣ ባለቤታቸው የመሣሪያውን መገኘት ባያስተባብሉም ከሌሎች ዜጎች እኩል የመዳኘት መብት እንደተከለከሉ እና ካቀረቧቸው አምስት ተከላካይ ምስክሮች መካከል የሁለቱ ብቻ ቃል ተሰምቶ ውሳኔ መሰጠቱን በቅሬታነት ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል አቃቤ ሕግ ይግባኝ ባሰማበት ተጓዳኝ የክስ ጭብጥ ላይ ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ቀጣይ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።
#ችሎት

2 months ago