(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሪፐብሊካን ፓርቲ የቅድመ ምርጫ የደገፏቸው እጩዎች ማሸነፋቸውን በ'ትሩዝ ሶሻል' ገጻቸው እያከበሩ ሲሆን፣ በተጓዳኝም አሌክስ ቪንድማን በዲሞክራቲክ ፓርቲ የቅድመ ምርጫ በአሜሪካ ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቶች አባል መሸነፉን በደስታ ገልጸዋል።
ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ "አጭበርባሪው ቪንድማን ዛሬ ምሽት በአክራሪ የግራ ክንፍ እብድ ተሸንፏል። ይሄ እንዴት ደስ ይላል???" በማለት ጽፈዋል።
በኪየቭ ተወልዶ ከቀድሞው ሶቭየት ህብረት የተሰደደው አይሁዳዊው ቪንድማን፣ ቀድሞ የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት አባል የነበረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2019 ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ያደረጉትን አወዛጋቢ የስልክ ልውውጥ ተከትሎ በትራምፕ የመጀመሪያ የክስ (Impeachment) ሂደት ላይ ለኮንግረስ ምስክርነት መስጠቱን ተከትሎ ነበር ስሙ በስፋት የታወቀው።
መንታ ወንድሙ በቨርጂኒያ የኮንግረስ አባል የሆነው ቪንድማን፣ ከዋና ተቀናቃኙ 16 እጥፍ የሚበልጥ የምርጫ በጀት ቢያሰባስብም፣ ፍልስጤምን የሚደግፉ ህጎችን በግዛት (ስቴት) ደረጃ እንዲጸድቁ በመግፋት በፓርቲዋ ውስጥ ስም ባወጣችው አንጂ ኒክሰን በቀላሉ ሊሸነፍ ችሏል።
ትራምፕ በሪፐብሊካን የቅድመ ምርጫዎች ያላቸውን ተጽዕኖ እና የድጋፍ ኃይል ለማሳየት የሚያደርጉት ጥረት አካል የሆኑት እነዚህ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች፣ በየምርጫው ምሽት በተከታታይ ሲወጡ ይስተዋላል። ፕሬዝዳንቱ "በዛሬው ምሽት ብዙ ታላላቅ ድሎች ተመዝግበዋል!!!" በማለትም አክለው ጽፈዋል።

2 months ago