በመጪው ረቡዕ ለስምንቱም አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በ4 ሺህ ጉባዔተኞች እንደሚጸድቁ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ውይይት ሲካሄድባቸው ለቆዩ አጀንዳዎች የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች በመጪው ረቡዕ እንደሚጸድቁ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ተናግረዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነሯ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተመካካሪዎች ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በራሳቸው እና በሌሎች ቡድኖች ምክረ ሀሳብ ላይ መወያየት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡
እንደ ኮሚሽነሯ ማብራሪያ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ተመካካሪ ቡድኖች የመረጧቸው ተወካዮች በቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ላይ ድግግሞሽ እና ተቃርኖ እንዳይኖር የማጠናከር እና የማጣጣም ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
ያጣጣሟቸውን ስራዎች ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለ500 ቡድኖች የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
ስምንቱም ቡድኖች በየራሳቸው አጀንዳዎች ላይ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ቡድኖችን ምክረ ሀሳብ ይረዳሉ፤ ባልተሳተፉባቸው ቡድኖች ምክረ ሀሳቦች ላይም ግብዓት ይሰጣሉ ብለዋል ኮሚሽነሯ በመግለጫቸው፡፡
ግብዓቱም ተሰብስቦ የመጨረሻ ሰነድ ይዘጋጃል፡፡
በዚህም ከነገ በስቲያ ወይም ረቡዕ በ4000 ጉባዔተኞች ይጸድቃል፡፡
Sheger Fm

2 months ago