(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የቀድሞው የቀዮቹ ሰይጣኖች እና የቶተንሃም አጥቂ ዲሚታር በርባቶቭ ማንቸስተር ዩናይትድ በኤሲ ሚላን 4-2 ስለመሸነፉ የሰጠው አስተያየት «ይህ ተራ ሽንፈት ብቻ አይደለም፤ በአንድ ጨዋታ ውስጥ የተገኙ ሁለት ትልልቅ ትምህርቶች እንጂ! በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሩበን አሞሪም በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ባስመዘገበው ድል ስለ ማርከስ ራሽፎርድ እና ኮቢ ማይኖ የተናገረው ነገር ሁሉ እውነት እንደነበር በተግባር አስመስክሯል።
"ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፍጹም ቅጣት ምት ካመከነ በኋላ ሳሙኤል ቹክዌዜ ጎል ቢያስቆጥርም፣ ማንቸስተር ዩናይትድ በዶርጉ አማካኝነት መሪነቱን መልሶ መያዝ ችሎ ነበር።
"ነገር ግን ሲሴ አቻ ሲያደርግ፣ ማይክል ካሪክ ቡድኑን ይታደጉታል በሚል ራሽፎርድን እና ኮቢ ማይኖን ወደ ሜዳ አስገባቸው፤ ሆኖም በተቃራኒው ጎንካሎ ራሞስ እና ሩበን ሎፍተስ-ቺክ በሶስት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ አሳፋሪ ሽንፈት አሸከሟቸው።
"ባለፈው የውድድር ዘመን የኦልድ ትራፎርድ ደጋፊዎች "ችግሩ አሞሪም ነው" ብለው እንዲያምኑ አድርገዋቸው ከነበሩት ከራሽፎርድም ሆነ ከኮቢ ማይኖ ቅንጣት ታክል ተጽዕኖ አልታየም።
"በሁለተኛ ደረጃ ይህ ጨዋታ ለሰር ጂም ራትክሊፍ፣ ለኢኒዮስ (INEOS) እና ለማይክል ካሪክ ትልቅ የዓይን መክፈቻ ነው። የዩሪ ቲለማንስ እና የሳንቶስ ዝውውር ብቻውን በጭራሽ በቂ አይደለም።
"ማንቸስተር ዩናይትድ እንደ ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ሊቨርፑል እና ቼልሲ ካሉ ክለቦች ጋር መፎካከር የሚፈልግ ከሆነ፣ ለሉክ ሾው ተተኪ ማስፈረም፣ እንዲሁም ማቴዎስ ኩኛ እና ብሪያን ምቤውሞ ብቻቸውን ስራውን መወጣት ስለማይችሉ ከቤንጃሚን ሴስኮ ጋር አብሮ የሚሰራ አጥቂ ማምጣት አለባቸው።
"ሌኒ ዮሮ፣ ዴ ሊክት እና ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በተደጋጋሚ ለጉዳት የሚጋለጡ ተጫዋቾች በመሆናቸው ክለቡ በሄቨን እና በሃሪ ማጓየር ላይ ብቻ ተማምኖ ሊዘልቅ አይችልም።
"ስለ ሴኔ ላመንስ ደግሞ በቅንነት መጠየቅ የምፈልገው ነገር አለ፤ ከአንድሬ ኦናና የተሻለ ምን የሰራው ነገር አለ? ባለፈው የውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች ገብተውበታል፤ በተመሳሳይ በርካታ ኳሶችን አድኗል። ጥሩ ግብ ጠባቂ የሚታወቀው ኳሶችን በማዳን ብቻ ሳይሆን መረቡን ሳያስደፍር (clean sheet በማስመዝገብ) ጭምር ነው።
"በዚህ አሁን ባለው የማንቸስተር ዩናይትድ ስብስብ ላይ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ስኬታማ መሆን አይችሉም፤ እኔም ለዚህ ውድቀት ተጠያቂ የማደርገው የክለቡን ባለቤቶች እንጂ አሰልጣኝ ካሪክን አይደለም!»

2 months ago