ጭስ አልባው የኢኮኖሚ ምሰሶ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ከአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎቿ አንዱ ሆኖ እያገለገለ ነው።
ዘርፉ ከጉብኝት መዳረሻና ከመዝናኛነት ባለፈ የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብና የሀገሪቱን ገፅታ በዓለም የሚያስተዋውቅ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው።
የቱሪዝም ዘርፍን ከአምስቱ የኢኮኖሚ አምዶች መካከል የተካተተው ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል ሀብት ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድል ለመቀየር በተያዘው ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ነው።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የተለያዩ መልክዓ ምድሮች፣ ብርቅዬ የዱር እንስሳት፣ ባለግርማ የተፈጥሮ ሐይቆች፣ ተራሮችና ልዩ ልዩ የተፈጥሮ ሀብቶች አሏት፡፡
በተጨማሪም ለሺህ ዓመታት የተገነባ ታሪክ፣ ቅርስና ባህል ባለቤት ናት።
ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ የተሰኙ ተነሳሽነቶችም የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸው የከተማ መዳረሻዎችን ጨምሮ ሌሎችም ቦታዎች ተገንብተዋል፡፡
የእነዚህ ሥራዎች አላማ ቦታዎችን ማስዋብ ብቻ አይደለም፤ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ የመስተንግዶ ተቋማትን፣ የመጓጓዣ አውታሮችንና ዲጂታል መሠረተ ልማትን በአንድ የቱሪዝም ሥነምህዳር ውስጥ ማስተሳሰር ጭምር እንጂ።
በዚህም ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻን የመሳሰሉ መዳረሻዎች በትልቅ ትኩረት የለሙ ሲሆን፤ እንደ ሐረር ጁጎልና ፋሲል ግንብ፣ የሶፍ ኡመር ዋሻን የመሳሰሉ ታሪካዊ ቅርሶችም ጥበቃና ማሻሻያ ተደርጎላቸው የቀደመ ይዘታቸውን ሳይለውጡ የቱሪስቶችን ቀልብ እየሳቡ ነው።
የመደመር የመንግሥት አቅጣጫ ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ የቱሪዝም አቅም ማወቅ ብቻ ሳይሆን በአግባቡ ማልማትና ለዓለም ማስተዋወቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በመሆኑም ቱሪዝም የመዝናኛ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የኢኮኖሚ ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሪ እድገት፣ የቅርስና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ራሷን ለዓለም የምታስተዋውቅበት የመታያ መድረክ ነው።
በእመቤት ሲሳይ

2 months ago