Logo
YenetaTube
ከእስራኤል ጋር መስማማትን እፈልጋለሁ !/ ሶርያ /

ደማስቆ ከዋሽንግተን ጋር በመተባበር ከእስራኤል ጋር በ1974 የተደረሰውን እና የአላሳድ መንግስት መዉደቅ ተከትሎ በእስራኤል የተጣሰዉን የድንበር መለያየት ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ ነች። ሲሉ የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል ሻይባኒ ተናገሩ ።

ሻይባኒ ከአሜሪካው አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ ጋር ባደረጉት የስልክ ጥሪ ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ሶሪያ “እ.ኤ.አ. በ1974 ወደ ተደረገው የመለያየት ስምምነት ለመመለስ ከአሜሪካ ጋር ለመተባበር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል ።

ይህ ሶርያ ዳግም እንዲከበር የጠየቀችዉ በጎላን ተራሮች ዙርያ የሚገኘዉ 235 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ከውትድርና ነፃ የሆነ የሁለቱ ድንበር ቦታ የዮም ኪፑር ጦርነት በኋላ በ1974 የተቋቋመው በእስራኤል እና በሶሪያ መካከል በተደረገው የመለያየት ስምምነት መሰረት በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች ለአስርት አመታት ሲታገል ቆይቷል።

ሆኖም የአሳድ መንግስት ሲወድቅ በሶሪያ ስርአቱ እስኪመለስ ድረስ ስምምነቱ ውድቅ እንደሆነ በመግለፅ እ.ኤ.አ.ዲሴምበር 8፣ 2024 ጀምሮ ወረራ መፈፀሟና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ድንበሩን በጎበኙበት ወቅት ስምምነቱ “ፈራርሷል” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን በወቅቱም ኢራን ሳኡዲ የእስራኤልን ወረራ ማዉገዛቸዉ ይታወሳል ።

በወቅቱ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስሜል ባጋሃይ በሰጡት መግለጫ “ይህ ጥቃት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን በግልፅ መጣስ ነው” ብለዋል።

የሳውዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ “በጎላን ሃይትስ የሚገኘው የግዛት ክልል መያዙ… እስራኤል የአለም አቀፍ ህግ ደንቦችን እየጣሰች መሆኑን እና የሶሪያን ደህንነት፣ መረጋጋት እና የግዛት ንፁህነቷን የመመለስ እድሏን ለማበላሸት መወሰኗን ያረጋግጣል” ሲሉ እስራኤልን አዉግዘዉ የነበረ ቢሆንም እስራኤል ከ300 በላይ ወታደሮቿን አስፍራበት ቆይታለች ።

ሁኔታዎች በዚህ መልክ ባሉበት ወቅት የሶሪያ መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አል ሻይባኒ በኩል የቀረበው ወደነበረበት የመመለስ ሀሳብ በእስራኤል በኩል ተቀባይነት ያገኛል ወይ የሚለው ጥያቄ እየተጠበቀ ቢሆንም እስካሁን ከቴላቪቭ የወጣ መረጃ የለም ።

የኔታ ትዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.