(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሩሲያ የተቀመጠውን 45 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት መቸገሩን ገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በውጭ አገራት ከሚያደርገው የትኬት ሽያጭ ገቢውን ለመሰብሰብ ተግዳሮቶች እየገጠሙት መሆኑን ጠቅሶ በአሁኑ ወቅት በሩሲያ 45 ሚሊዮን ዶላር እንዳለው አስታውቋል፡፡ ይሁንና በዩክሬይን ጦርነት የተነሳ የአውሮፓ አገራት በጣሉት ማእቀብ ይህንን ገንዘቡን ማግኘት እንዳልቻለ አስረድቷል፡፡
ይህ በሞስኮ የሚገኘው የአየር መንገዱ ገንዘብ በጠቅላላው ለማግኘት ከተቸገረው 90 ቢሊዮን ዶላር ግማሽ ያህሉን የሚሸፍን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኮሜርሺያን ኦፊሰር አቶ ለማ ያዴቻ ለሪፖርተር መፅሄት ሲናገሩ ‹‹በሩሲያ ላይ በተጣለው ማእቀብ የተነሳ ከባንክ ወደባንክ መደበኛ የገንዘብ ዝውውር ማድረግ አልቻልንም›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ቀደም ሲል በሞስኮ ከሚገኘው አካውንታችን በቀጥታ ወደአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ የተባበሩት አረብ ኤመሬትስ፣ ጀርመን ወይንም አዲስ አበባ ወደሚገኙ የባንክ አካውንታችን ማስተላለፍ እንችል ነበር፡፡
አሁን ግን ሲቲ ባንክን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆኑ አለም አቀፍ ባንኮች ከሩሲያ ባንኮች ገንዘብ መቀበልም ሆነ መላክን ከልክለዋል›› በማለት ገልፀዋል፡፡ በሩሲያ ውስጥ የሚገኘውን ይህንን 45 ሚሊዮን ዶላር ለማስለቀቅ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከዲፕሎማሲያዊ ልኡካን ጋር እየሰሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ፕሬስ ሰክሪተሪ ሊዮኔል ባርዘንዩክ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ኤምባሲው በዚህ ላይ አስተያየት ያለመስጠት አቋም እንዳለው ገልፀዋል፡፡

2 months ago