ሙስናን መዋጋት፤ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በመደመር መንግሥት መሪነት የተለያዩ የልማትና የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች።
በዚህም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ በማድረግ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋት እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
ትውልድን ታሳቢ ባደረገው የልማት አቅጣጫ ገና ከጅምሩ እጅግ አስደናቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነውጰ፤ ነገር ግን የሕዝብ ሀብት በሙስናና በሌብነት ከባከነ ይህንን የልማት ጉዞ ወደ ኋላ ይጎትታል፡፡
በዚህ መሠረት ሙስናን መዋጋት ከሌሎች የልማት ሥራዎች ተለይቶ የሚታይ ጉዳይ ሳይሆን የልማት ዘላቂነትን የማረጋገጥ ዋነኛ ተግባር ነው።
ለሕዝብ ጥቅም የሚውል መሰረተ ልማትን ለመገንባት የሚመደብ በጀት የግል ጥቅምን በሚያስቀድሙ ሙሰኞች ሲመዘበር የሀገር ሀብት የማመንጨት አቅም ይቀንሳል።
በተለይም በግዥ፣ በጨረታ፣ በፕሮጀክት አፈጻጸምና በበጀት አጠቃቀም የሚፈጠር ሙስና ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ ሙስና ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የልማት ዕድልንም ያሳጣል።
በተጨማሪም ሙስና የኢንቨስትመንት እድሎችን የሚያጠብብ የልማት ጸር በመሆኑ ሙስናን መቆጣጠር የሕዝብ ሀብትን ከመጠበቅ ባሻገር የኢንቨስትመንት እምነትን የማጠናከሪያ መሳሪያም ነው።
በኢንቨስትመንት ላይ የሚሰማሩ አካላት መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱበትን ሀገር ሲመርጡ የገበያ ዕድልን ብቻ ሳይሆን የሕግ የበላይነት፣ የተቋማት ተጠያቂነት፣ የአሠራር ግልጽነትና የውሳኔ ተገማችነትን ከግምት ያስገባሉ፡፡
በዚህም በተቋማት ውስጥ ጉቦና ሙስና ተስፋፍቷል የሚል ግንዛቤ ከተፈጠረ አልሚዎች በኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ስጋት ያድርባቸዋል፡፡
ሙስና በአንዲት ሀገር ልማትና የእድገት ጉዞ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከሰነድ ባለፈ በዝቅተኛ ጥራት፣ በዘገየ ፕሮጀክትና በጠፋ የልማት ዕድል ይገለጣል፡፡
የልማት ፕሮጀክቶች በሙስና ምክንያት ጥራታቸውን ጠብቀው በወቅቱ ካልተጠናቀቁ ተጎጂው በመጨረሻ ሕዝብና ሀገር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ስብራትና የጥፋት መንገድ የሆነው ሌብነት ካልተገራ በስተቀር ለምናስበው የመበልጸግ ራዕይ እንቅፋት ነው፡፡
በዚህም የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን የልማት ጉዞና የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሰናክል ሙስናን ለመዋጋት ጠንካራ ርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ

2 months ago