Logo
Getu Temesgen
በሰሜን ሸዋ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም በመሬት መንሸራተት 14 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ
#ethiopia | አዲስ አበባ – በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው ታሪካዊው የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በደረሰ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ 14 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 5 ሰዎች ደግሞ የከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

እንደ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት መረጃ፣ አደጋው በክረምቱ ወቅት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የተከሰተ ሲሆን፣ በወቅቱ ለጸበል፣ ለሱባኤ እና ለንግሥ በገዳሙ የተገኙ ምዕመናን ላይ ጉዳቱ ደርሷል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በአደጋው ስፍራ በመገኘት ለሕይወታቸው ላለፉት የፍትሐት ጸሎት አድርገው፣ ለተጎዱትና ለተጨነቁት ምዕመናን አባታዊ ቃለ በረከትና የማጽናኛ ትምህርት ሰጥተዋል።

ሀገረ ስብከቱ በመግለጫው በአደጋው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጾ፣ ለሞቱት ዕረፍተ ነፍስ፣ ለተጎዱት ፈጣን ፈውስ፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናት ተመኝቷል።

የአደጋው መንስኤ ከከፍተኛ ዝናብ ጋር የተያያዘ የመሬት መንሸራተት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በቦታው ያሉ አስፈላጊ የድጋፍና የእርዳታ ሥራዎች መቀጠላቸው ተጠቁሟል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አቡ ቀለምሲስ ሚዲያ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.