Logo
SeledaPost
ኤችአይቪ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው
‎
‎አሁን ላይ በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የኮንዶም ዕጥረት መኖሩም ተነስቷል።
‎
‎ዕድሜያቸው ከ14-24 የሆኑ ሴቶች በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለኤችአይቪ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ መሆናቸው ተገልጿል።
‎
‎በአገራችን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል ተብሏል።
‎
‎አሁን ላይ 7መቶ ሺህ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል የተባለ ሲሆን፥ቁጥሩ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ሰምተናል።

‎ይህን የሰማነው የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ይህን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።
‎
‎ኔፕ ፕላስ በኤችአይቪ ህመም ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ተቋም ሲሆን፥ ምስረታው ወደ 22 ዓመት እየተጠጋው ነው።
‎
‎በዚህ ኔትወርክ ስር የተቋቋሙ ከ5መቶ በላይ ማህበራትን የያዘ መሆኑ ሲገለፅ፥ በዋናነት አሁን ላይ በንቃት የሚንቀሳቀሱት እና የግሎባል ፈንድ ተጠቃሚ ማህበራት ቁጥር 1መቶ29 ነው።
‎
‎የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ፥ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
‎
‎ይህ ጉባዔ እየተዘነጋ ስላለው ነገርግን ዛሬም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው የኤችአይቪ ህመም ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥበት ነው።
‎
‎ድርጅቱ ለሁለት ጊዜ ያህል "Stigma index research" ማሰራቱን ገልጾ፥ ሶስተኛ ዙር ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

‎በጉባኤው ላይ የጤና ሚኒስቴር ሀላፊዎች ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከኔፕ ፕላስ ማህበራት የተወከሉ በአጠቃላይ 1መቶ20 እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
‎
‎Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.