(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ ‹‹300 ፓትሪዮት ሚሳኤል በአስቸኳይ እንዲሰጠን ጠይቄያለሁ›› አሉ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ከአስክዮስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፕሬዝደንት ትራምፕ 300 ፓትሪዮት ሚሳኤል እንዲሰጧቸው መጠየቃቸውን ገለፁ፡፡ ሲናገሩም ‹‹በዩክሬይን የሀይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ የፓትሪዮት አየር መከላከያ በአስቸኳይ እንዲቀርብልን ጠይቄያለሁ›› ብለዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹የዩክሬይን የፓትሪዮት ሚሳኤል ክምችት እየተሟጠጠ ነው፡፡ ይህንን ካላገኘን ከባለስቲክ ሚሳኤል ራሳችንን መከላከል አንችልም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኬይቭ ላይ የሚደረገውን የሩሲያ ጥቃት መከላከል ያልቻልነው ለዚህ ነው›› ካሉ በኋላ ‹አስቸኳይ የክረምት ፓኬጅ›› እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል፡፡ አክለውም ‹‹ይህ ችግር በክረምቱ ካልተፈታ የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃቶች የዩክሬይንን ሀይል ማመንጫዎች በማወደም ሚሊዮኖችን ካለማሞቂያ በማስቀረት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል›› ያሉት ዘለንስኪ በመጪው የ3 ወራት ክረምት በእያንዳንዱ ወር 100 በጠቅላላው 300 ፓትሪዮት ሚሳኤል የግዴታ እንደሚያስፈልጋቸው አስረድተዋል፡፡
ምክንያቱም ሩሲያ በወር ውስጥ በአማካኝ ከ30 እስከ 40 ባለስቲክ ሚሳኤሎችን እንደምትጠቀም ገልፀዋል፡፡ ትራምፕ ለጥያቄያቸው መልስ ለመስጠት ጥረት እንደሚያደርጉ እንደገለፁላቸው ተናግረውም ይሁንና የተባለውን ለመፈፀም አስቸጋሪ መሆኑን እንዳስታወቁ አስረድተዋል፡፡ አሜሪካ ከኢራን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት ለራሷ በርካታ ፓትሪዮት ሚሳኤል የምትፈልግ መሆኑ እንደተገለፀላቸው አስታውቀዋል፡፡ ዘለንስኪ እንዳሉት ሌላኛው አማራጭ የፓትሪዮት ሚሳኤልን የማምረት ፈቃድ ለዩክሬይን እንዲሰጣት ማድረግ ነው፡፡ ይሁንና ፈቃዱ ቢሰጣት እንኳ ለማምረት ከአንድ እስከ አምስት አመት የሚጠይቅ መሆኑ እንደተገለፀላቸው ያስታወቁት ዘለንስኪ ጨምረውም ‹‹ያም ሆነ ይህ ፓትሪዮት ያስፈልገናል›› በማለት በቃለ ምልልሱ አስታውቀዋል፡፡

9 days ago