የኢሰመጉ 158ኛ ልዩ መግለጫ፡
በምስራቅ አርሲ ዞን በሃይማኖትና ማንነት ላይ ያነጣጠሩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መቀጠላቸውን ኢሰመጉ ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሐምሌ 2018 ዓ.ም ባወጣው 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ሃይማኖትንና ማንነትን መሰረት ያደረጉ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን ገለጸ።
ተቋሙ ከመጋቢት 3 እስከ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው የምርመራ ወቅት በተሰበሰቡ አስረጂዎች፣ በዞኑ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች በዋናነት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ የግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የእገታ፣ የመፈናቀል እና የንብረት ውድመት ድርጊት መፈጸማቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
የጥቃቶቹ ስፋትና የደረሰው ጉዳትበኢሰመጉ የምርመራ ግኝት መሰረት በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ በምስራቅ አርሲ ዞን ወረዳዎች በግድያ ህይወታቸውን ያጡ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር የሚከተለውን ይመስላል፦
መርቲ ወረዳ፦ 117 ሰዎች
-ሽርካ ወረዳ፦ 116 ሰዎች
-ጀጁ ወረዳ፦ 101 ሰዎች
-ሮቤ ወረዳ፦ 47 ሰዎች
-ጉና ወረዳ፦ 26 ሰዎች (በአንድ ጉድጓድ የተቀበሩ 5 ሰዎችን ጨምሮ)
-ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፦ 20 ሰዎች
-አሰኮ ወረዳ፦ 5 ንጹሃን ዜጎች እና
4 የመንግስት ሚሊሻዎች
አርሲ ሲሬ ወረዳ፦ 3 ሰዎች
በተጨማሪም በህጻናትና አረጋውያን ላይ የከፋ የአካል ጉዳት መድረሱን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ በጉና ወረዳ በፈጸመ ጥቃት የ4 እና የ8 ዓመት ህጻናት በጥይት መመታታቸውንና የአንዱ ህጻን እግር ሊቆረጥ መቻሉን በአብነት ጠቅሷል።
እገታ፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት
ኢሰመጉ ባቀረበው ዝርዝር መረጃ መሰረት፦
እገታ፦
በሮቤ ወረዳ 156 ሰዎች፣
በጀጁ 182 ሰዎች፣
በምርቲ 29 ሰዎች እንዲሁም
በሽርካ 39 ሰዎች ታግተው ከፍተኛ የገንዘብ ransom የተጠየቀባቸው ሲሆን
በርካቶቹ በገንዘብ ቢለቀቁም የበርካታ ታጋቾች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን አይታወቅም።
መፈናቀል፦
በጥቃቱ ስጋት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፤ ከጀጁ ወረዳ 6,216፣ ከሽርካ 3,746፣ ከአሰኮ 2,133፣ ከሮቤ 1,270 እና ከመርቲ 1,036 ሰዎች ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።
የንብረት ውድመት፦
በርካታ አብያተ ክርስቲያናት መዘረፋቸውንና መቃጠላቸውን (ለምሳሌ በ101 ዓመት ዕድሜ ያለው የጠለታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን)፣ ቤቶች መፍረሳቸውንና መቃጠላቸውን እንዲሁም በርካታ የጋማና የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውን ሰነዱ ያመላክታል።
የህግ ግዴታዎችና የኢሰመጉ ጥሪ
ኢሰመጉ ድርጊቶቹ በስልታዊና በተስፋፋ መልኩ በሲቪል ህዝብ ላይ የተፈጸሙ በመሆናቸው በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች (Crimes Against Humanity) ባህሪ ያላቸው መሆኑን በመጠቆም፣ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መንግስታት የሚከተሉትን እርምጃዎች እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፦
ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፦ በጥቃቱ የተሳተፉ ታጣቂዎችንና ሀላፊነታቸውን ያልተወጡ የጸጥታና የአስተዳደር አካላትን በአስቸኳይ ለህግ ማቅረብ።
ሰብዓዊ እርዳታና መልሶ ማቋቋም፦ ለተፈናቀሉ ዜጎች ህክምና ማቅረብ እንዲሁም በይስሙላ ሳይሆን በዘላቂ ሰላም ወደ ቀያቸው የሚመለሱበትን መንገድ ማመቻቸት።
የፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት፦ የክልሉ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ካልቻለ፣ በህግ በተደነገገው መሰረት (አዋጅ ቁጥር 359/2003) የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት የዜጎችን ህይወት እንዲታደግ።

2 months ago