ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባችው ግዙፍ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ!!
የወርቅ ግዥን ወደ ንግድ ባንኮች ለማዘዋወር ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የአገሪቱ የመጀመሪያው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ በመጪው አንድ ወር ውስጥ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር አስታወቁ።
ገዥው ይህንን የገለጹት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሰባተኛ ስብሰባው የገመገማቸውን የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሁኔታዎች፣ ያቀረባቸውን ምክረ ሐሳቦችና የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ያፀደቃቸውን የፖሊሲ ውሳኔዎች አስመልክቶ ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሲሰጡ ነው።
ከአፍሪካ አልፎ ከዚያ በላይ በግዙፍነቱ የሚጠቀስ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ (ሪፋይነሪ) ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት እዮብ (ዶ/ር)፣ ፋብሪካው በመጪው አንድ ወር ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ፣ ለአገሪቱ የወርቅ ገበያ እጅግ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
የአገር ውስጥ የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ወጪን በከፍተኛ ደረጃ ከመቀነሱም በላይ፣ ቀደም ሲል ወርቅ ወደ ውጭ በመላክ እንዲነጠር ተደርጎ ከዚያ በኋላ ለሌሎች ክምችት በዶላር የመሸጠን አሠራር ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀር ነው ብለዋል። በመሆኑም ፋብሪካው ለኢትዮጵያ የወርቅ ገበያ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቀጣናው ትልቅ አቅም ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልጸዋል።
ገዥው ይህንን ቢሉም ፋብሪካው የት አካባቢ እየተገነባ እንዳለና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ዘገባው የኢትዮጵያ ሪፖርተር ነው
Seledadotio

3 months ago