(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ በዋና ዋና የአሜሪካ እና የዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ (ዩኤኢ) ከተሞች በሚገኙ መደበኛ ያልሆኑ የምንዛሬ ገበያዎች፣ የአንድ አሜሪካን ዶላር የመግዣ ዋጋ 181.60 የኢትዮጵያ ብር መድረሱ ታውቋል። ይህ ከፍተኛ የምንዛሬ ፍላጎት እና የጥቁር ገበያ ንረት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚከተለው የጉምሩክ እና የታክስ ፖሊሲ ጋር ቀጥተኛ ትስስር እንዳለው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) በቅርቡ ባወጣው ሂሳዊ ሪፖርት አጋልጧል።
አይ.ኤም.ኤፍ (IMF) ይፋ ባደረገው 5ኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ የግምገማ ሪፖርት ላይ እንዳስገነዘበው፣ በመንግሥት በኩል የተጣሉት "የተጋነኑ" እና "የዘፈቀደ" የጉምሩክ ቀረጥ ተመኖች ሀገሪቱን ለከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ እያጋለጧት ይገኛሉ። ሪፖርቱ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ እነዚህ ምክንያታዊ ያልሆኑ የታክስ ጫናዎች ነጋዴዎች የውጭ ምንዛሬን በህገ-ወጥ መንገድ (በጥቁር ገበያ) እንዲፈልጉ ዋነኛ ገፊ ምክንያት ሆነዋል።
ለዚህ የኢኮኖሚ መዛባት እና የጥቁር ገበያ መስፋፋት በዋነኝነት አስተዋጽኦ ያደረጉት የመንግሥት የታክስ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው:-
▪️ እስከ 35 በመቶ የሚደርሰው ከፍተኛ የጉምሩክ ቀረጥ
▪️የ 10 በመቶ ተጨማሪ ቀረጥ ወይም ሱር ታክስ
▪️ ከ 5 በመቶ እስከ 500 በመቶ የሚደርሰው እጅግ የተጋነነ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ
እነዚህ የተደራረቡ የታክስ ጫናዎች ሕጋዊውን የንግድ ሥርዓት በማዳከም፣ ነጋዴው ማትረፍ ወደሚችልበት የኮንትሮባንድ አማራጭ እንዲያዘነብል ማስገደዳቸውን ተቋሙ በሪፖርቱ አብራርቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍ በማሰብ አዳዲስ የታክስ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማጽደቁን ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) በሪፖርቱ አወድሷል። በተጨማሪም በቀጣዮቹ ጊዜያት መንግሥት አዲስ የታክስ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን ሪፖርቱ ጠቁሟል። በዚህም መሠረት፣ መንግሥት በነዳጅ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ ታክስ የሚጥል ሲሆን፣ የዚህ እርምጃ ዋና ዓላማዎች የመንግሥትን የገቢ አሰባሰብ አቅም ከፍ ማድረግ እንዲሁም ከነዳጅ ነጻ የሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አጠቃቀም በሀገር ውስጥ በስፋት ማበረታታት መሆኑ ተገልጿል።
እነዚህ አዳዲስ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የጥቁር ገበያውን የምንዛሬ ጫና እና የኮንትሮባንድ ንግድን ምን ያህል ሊገቱት ይችላሉ የሚለው በቀጣይ የመንግሥት የተግባር አፈጻጸም ላይ የሚመዘን ይሆናል።

3 months ago